የክፍለ ዘመኑ ባለተአምራት ባህታዊያን አጥማቂዎች የቤክርስቲያን ፈተናዎች
“የተመረጡት እንኳ እስኪያስቱ ድረስ ታላላቅ
ተአምራትንና ድንቅ ስራን ይሰራሉ” /ማቴ.24፥24/
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ውዱስ አሀዱ አምላክ አሜን፡፡
መግቢያ
እግዚአብሄር አምላክ ለእያንዳንዱ
ሰው እንደየ ተሰጦው እንዲኖር ኖሮም ለዘላለም እንዲድን በዚህ ምደር የሚኖርበትን እድል ፈጠሮለታል እያንዳንዱ እንደየአቅሙ እንዲኖርና
ማሰብ በሚችለው በሚገባው አእምሮው እንዲያስብ ነፃ ፈቃድ ከሀይማኖት ጋር ሰጥቶታል አንዱን ጥሎ አንዱን አንጠልጥሎ መሄድ የሰው
ስሁትነት ወይም የነጻፈቃድ ማሳያ መሆኑ ነው እንጂ ሰው በነፃነት አምላኩን እያመለከ በተሰጠው ፀጋ የመንግስቱ ወራሽ የክብሩ ቀዳሽ
እንዲሆን በአርአያ ስላሴ የተፈጠረ ልዩ ፍትረት ነው፡፡ ሰው በተቻለው እና በወደደው እንዲኖር ብቻውን መኖር ለማይችለው እረዳትን
ፈጥሮ የሰጠው እግዚአብሄር የሰው ኹሉ መጀመሪያ በኾነው አዳምን ከፈጠረ በኋላ፣ “ሰው ብቻውን ይኾን ዘንድ መልካም አይደለም፤ የምትረዳውን
በአጠገቡም የምትኾን የምትስማማውን ረዳት እንፍጠርለት፤” በማለት የሰጠው ቃል የሰው ልጆች ኑሮ በብቸኝነት ላይ እንዳልተመሠረተ
እንዲሁም የዓለሙ የኑሮ ቀንበር በብቸኝነት ሊታለፍ ሚከብድ መሆኑን የሚያስረዳን ሲሆን ከዚኽ ዓለም ጣጣና፣ ሐሳብ እርቆ፣ እግዚአብሔርን
በሙሉ ልብነት ለማገልገል፣ መከራውን ታግሦ ለአገልግሎት ለመጋደል ብሕትውና እና ምንኵስና ደግሞ በገዳመ ቆሮንቶስ ባርኮ በብህትውና
ቢኖር በፈቃዱ እየታገለ ከዲያቢሎስ ጋር እየተዋጋ በረከትን ቅድስናን የሚያሰጥ በገዳም በምንኩስና መኖር ለሚፈልጉ እንደፈቃዳችው
እንዲኖሩ እየመራቸው ያከበራቸው እግዚአብሄር ለእያንዳንዱ ስርአት ሰርቶ እንዲጠቀሙበት በአባቶቻችን የተገለጠ እጅግ ጠቃሚ የፍጹማን
የጽድቅ መሥመር እንደኾነ ልብ ይሏል፡፡ (ማቴ.19፥10-13)
እነዚህ
የህይወት ጉዞዎች ግን ለእያንዳንዳቸው የራሳቸው የሆነ ስርአት የአኗኗር መርህ ያላቸው ሲሆን ሶስቱም በእግዚአብሄር ዘንድ እንደስርአቱና
እንደ ህጉ ለተጠሩ ለሚኖሩበት የተፈቀዱ የተቀደሱና የተወደዱ ለሰው ልጆች የተሰጡ የፅድቅ መስመሮች ናቸው፡፡እንደመንደርደሪ ያክል
ብንመለከታቸው
1.
በትዳር ተወስኖ መኖር ፤ የዚህ አለም ኑሮ አድካሚና ከባድ በመሆኑ እግዚአብሄር አምላክ ፍጥረታትን ወንድና ሴት አድርጎ ከፈጠራቸው
በኋላ ወደ አዳም አምጥቶ ስም እንዲያወጣላቸው አደረገ አዳምም አወጣላቸውና ከኔ በቀር ብቻውን የተፈጠረ የለም፤ሁሉም ስጋዊ ደማዊ
እንስሳት አራዊት ሴት እና ወንድ ሆነው ነው የተፈጠሩት ብሎ አዘነ፡፡ በዚህ ጊዜ እግዚአብሄር ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም
አይደለም ብሎ እረዳት እንፍጠርለት አለ፡፡ከፈጠረው በኋላ የመጀመሪያውን ማደንዘዣ እንቅልፍ በአዳም ላይ ያደረገው እግዚብሄር እረዳት
ትሆነው ዘንድ ሄዋንን እንዲሰጠው የተከናወነ ሄደት ነበረ ፡፡ በእንቅልፍና ሰመመን(በመንቃት) መካከል እንዳለ ቢነቃ እንዳያመው
ተኝቶ ሳለ ቢፈጥራት ባእድ እንዳያደርጋት አድርጎ ከጎድኑ አንዲት አጥንት ወስዶ ቀርፆ ሴት አድርጎ እነኋት እረዳት ትሁንህ አለው፡፡
አንድም የሁለቱ ተዋህዶት በመኝታ አንድ ስጋ ይሆናሉና ፈጥሮ ሰጠው እሱም ተቀበለ አእምሮውን ለብዎውን ሰጥቶታልና አንድም አዳም
ነብይ ነውና ይህች አጥንት ከአጥነቴ ስጋዋም ከስጋየ ናት አለ፡፡ እርስዋ ከባልዋ ተገኝታለችና
ሚስት ትሁነኝ ብሎ ወሰዳት ፡፡ አንድ ስጋም ሆኑ ይላል መፅኀፍ/ዘፍ2፡23/ይህ ታላቅ ምስጢር ነው፡፡ በዚህም እየተረዳዱ አምላካቸውን
ደስ ያሰኛሉ፡፡ እንግዲህ አንዱ አለምን ከሚያሳልፉበት ህግ ይህ ህገ እግዚአብሄር ነው፡፡
2.
ብህትውና፡፡ ባሕታዊ ማለት ራሱን ለቅድስና ለተጋድሎ
አዘጋጅቶ ከላመ፤ ከጣመ ተቆጥቦ መኖርን የሚጠይቅ በገዛ ፈቃድ የሚደረግ የክርስትና ኑሮ ዘይቤ ነው። ሥርዓተ ብሕትውና የተጀመረው
የአዳም ሰባተኛ ትውልድ በሆነው በሔኖክ ነው። በብሉይ ኪዳን እነ ኤልያስ በጌታ መምጫ መንገድ ጠራጊ የነበረው ዮሐንስ በኋላም ደግሞ
በሀዲስ ኪዳን ብህትውናን የመሰረተው አባ ጳውሊ በምነና ህይወት ተጠቃሽ ናቸው። የሰዎቹ መነሳት ብቻ ሳይሆን ምነናን በተግባር አሳይተው
ያለፉም ናቸው። ባሕታዊ ወይም ብሕትውና ራስን ለእግዚአብሔር መንግስት ጃንደራባ አድርጎ ማቅረብ ነው። ቅዱስ ጳውሎስ “ሁሉን እያጡ
መከራን እየተቀበሉ እየተጨነቁ የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ” ያለውን ኑሮ የኖሩት ናቸው። ይሕ መንፈሳዊ ሕይወት ከምናስበው
በላይ ቅድስናን የተላበሰ ትልቅ ገድል፤ ትሩፋት ያለበት ነው። ብሕትውና፦ በፈቃድ ላይ ተመሥርቶ ባሕታዊነት፣ ዝጉሐዊነት፣ በዓለም
ዘንድ ሞቶ፣ ዓለምን ገድሎ፣ዓለምን ንቆ ከንቱ አድርጎ፣ ጠልቶ፣ አኮስሶ፣ ነቅፎ አጸይፎ፣ ክዶና ጥሎ፣ ልብስን አንጠልጥሎ መሔድ፤
ብቸኝነት፣ ፍጹም ምናኔ፣ ከዓለምና ከዘመድ መለየት፣ መነጠል፣ የዘመድ ድኻ መኾን ነው፡፡ ብቸኛ ከመኾን የተነሣ ማዘን፣ማልቀስ፣
መፍራት መጨነቅ ነው፡፡ ግርማ ሌሊቱን፣ ድምፀ አራዊቱን፣ ጸብአ አጋንንቱን ታግሦ፣ በዱር በጥሻ፣ በገደል በዋሻ በጸሎት ተጸምዶ፣
ከመንደር ከከተማ ተወግዶ መኖር ነው፡፡ ይህም በወንጌል የጸደቀ ፍጹም የፈቃድ ሕግ ነው፡፡ ብሕትውና ለብቻ መሆንን ይዘወተራል።
ለምሳሌ ዋሻ ውስጥ መሰወር ግንድ ወይም ዛፍ ላይ ወጥቶ ሳይወርዱ መኖርን ይመርጡ ነበር። በወቅቱ ምግብ ባለመመገብ ውሓ ባለመጠጣት
ያሳልፉ እና ይሞቱም ስለነበር በምነናው ሕይወት፡ ራስን በምግብ እና ውሐ ማጣት መሞት ትክክል አይደለም በሚል የኑሮ ዘይቤው ብዙም
አልተደገፈም። በተለይ (ኤሴያውያን የሚባሉ ቡድኖች የሚመሩት የነበረ ሕይወት) ። ሊቁ አርጌንስም ከሊቅነት ባሻገር ምናኔ ትልቁ
መታወቂያው ነበር። በዚህም ራሱን ጀንደረባ አድርጎ ስለ ነበር ከተነቀፈበት ተግባር አንዱ ይሕ ነበር። ባሕትውያን በቤተክርስቲያን
የቆየ ሕይወት ሲሆን። ከምናኔ ባሻገር እግዚአብሔር ሲልካቸው ከበረሃ እንደ ኤልያስ ብቅ እያሉ ለንጉሡም ፤ለካህናቱም መልክት አስተላልፈው
ወደ በዓታቸው ይመለሳሉ።
3.
ምንኵስና፦ መነኮስ ማለት ዘርህቀ እምዓለም ወተፈልጠ እምሰብእ ማለት ነው1፡፡
ከምንም ወይም ከማንም ግዴታ ውጭ፣ በግል ፈቃድ ላይ ተመሥርቶ
መነኵሴ መኾን፣ በአክሊለ ሦክ ምሳሌ ጌራ መድኃኒት ቆብ መጫን፣ አስኬማ መልበስ፤ ሰውነቴን ለእግዚአብሔር ገንዘቤን ለማኅበር ብሎ
ቃል ኪዳን መግባት፣ ከዚኽ ዓለም ሀብት፣ ዘመድና ወንድም መድኸየት ነው፡፡ ንጽሕ መጠበቅ ከሴት መራቅ፣ በባተሌነት በድንግልና ነፍስ
መኖር ነው፡፡ ገዳማዊ፣ ባሕታዊ፣ መልአካዊ ኹኖ መኖር ነው፡፡ ምንኩስና እንደነ እንጦንዮስ ገንዘብ ሀይልህ የት አለ፤ ገንዘብ እወቀትህ
የት አለ ፍጥነት የት አለ; ገንዘብ ሁሉም የሌሉት ዋስትና የማይሆን መሆኑን ቢያውቀው ሁሉንም ለነዳያን ሰጥቶት ወደ ገዳም መሄዱን
ይናገራል፡ መነኩሴ ገንዘብ ላፍራ ሹመት ልሾም የማይል ሁሉን ትቶ የተሰደደ ነውና፡፡ ብሕትውናም ኾነ ምንኵስና፣ በምሥጢር አንድ
ሲኾኑ፣ ዓላማቸውም፣ በዓለም ከሚሠራው 15ቱ ፈቃዳተ ሥጋ ለመራቅና ለዘጠኙ ፈቃዳተ ነፍስ በመገዛት ፍጹም ሆኖ ለመኖር ነው፡፡ ከሰው
ልጆች ጥንተ ጠላት ከዲያብሎስ ጋራ የሚደረገውን ግብግብ ተቋቁሞ ድል አድራጊ በመኾን የመንግሥተ እግዚአብሔር ተሸላሚ ለመኾን ነው፡፡
ኅሊናን ከሥጋዊ ሐሳብ ለመሰብሰብ፣ እግዚአብሔርን በፍጹም ልብ ለማገልገል ፤ምድራውያን መላእክት ሰማያውያን ሰዎች ለመኾን ነው፡፡
የምንኵስና ተግባርና አኳኋንም፦ በዓት ይዞ ከገዳም ገብቶ፣ ጾምና ጸሎት ቀዊምና ስግደት ነው፡፡ አብሮ መሥራት አብሮ መብላት ነው፡፡
ግፍዓ ወሞተ ወልደ እግዚአብሔርን እያስታውሱ፣ የራስንና የወንድምን ኃጢአት እያሰቡ፣ ከሣቅ ከሥላቅ፣ ከዋዛ ከፈዛዛ ተቆጥቦ፣ የሞቀ
የደመቀ ሳይለብሱ፣ በአንክሮ በተዘክሮ፣ በአርምሞ በተጸምዶ በገዳም መኖር ነው፤ እየተዘዋወሩ ማስተማር፣ ማጥመቅ፣ ማቊረብ ነው፡፡
ምንኵስና፦ በዓትን ከገዳም ከአኃው መነኰሳት ጋራ በማድረግ፣ ለጾም ለጸሎት፣ ለቀዊም ለስግደት መትጋት ነው፡፡ እግዚአብሔርን ፈሪ
ሰዎችን አክባሪ መኾን ነው፡፡ በማኅበር ሥራ አለመለገም፤ ቅንና ትሑት መኾን፤ ለአበ ምኔት መታዘዝ ነው፡፡ በግብርና ሥራ ካልተሠማሩ
በቀር፣ በቀን አንድ ጊዜ ብቻ በማኅበር መመገብ ነው፡፡ ምጽዋትንና ቸርነትን ማዘውተር፣ መውደድ ነው፡፡ ለጾርና ለመነቃቀፍ ምክንያት
እንዳይኾኑ፣ ትጋትንና ንቃትን ለማግኘት፣ አስኬማን ወይም ቅናተ ዮሐንስን ሳያወልቁ ለብቻ መተኛት ነው፡፡ ካልታመሙ በስተቀር ሥጋን
አለመብላት፣ ጠጅ ወይም ሌላ የሚያሰክር መጠጥ አለመጠጣት፣ ደግሞም ብቻዬን ወይም ብዙ ስጡኝ ለማለት አለመከጀል፤ ከመሬት ላይ መተኛት
ነው፡፡ ለፈውስ ደዌ፣ በአበም ምኔቱ ተፈቅዶለት ካልኾነ በስተቀር ከሙቅ የገላ መታጠቢያ ቤት ገብቶ አለመታጠብ ነው፡፡ ማኅበር እንዳይሸበር
ወይም እንዳይነቅፉት፣ ከልክ ያለፈ ልቅሶና ጮኾ መጸለይ አይፈቀድም፡፡ ገዳም ገብቶ በማኅበር ከኖረ በኋላ የግል ሥራ አለመሥራት፣
የግል ጥሪት አለማበጀት፣ ንግድ አለመነገድ፣ አለማስነገድ፣ አራጣም አለመቀበል ነው፡፡ ነፍስን የሚጎዳ ክፉ እንዳያሳስብ፥ ክፉ ከመናገር፣
ክፉ ከማየት፣ ክፉ ከመስማት መከልከል ነው፡፡ መነኵሴ ከገዳም ገብቶ በማኅበር መኖር ይገባዋል፤ ምክንያቱም ብቻውን የሚኖር ከኾነ፣
“ሰዓት አለፈብኽ፤ ትሩፋት ጎደለብኽ” የሚለው አያገኝምና፤ ደግሞም፣ የሌላው በረከት አይደርሰውምና፤ እርሱም ለሌላው አይተርፍምና፣
ለሌላውም አርኣያ አይኾንምና ነው፡፡ ብሕትውናም ኾነ ምንኵስና፣ በደናግላንና በመናንያን መመኪያ በጌታችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ
ክርስቶስ በገዳመ ቆሮንጦስ ተባርኮ የጸደቀ ነው /ማቴ.4፥ 1-11፤ ሉቃ.21፥37/፡፡ የብሕትውና እና የምንኵስና ኑሮም፣ በቅዱሳን
ሐዋርያት ተጠናክሯል፤ ተስፋፍቷል፡፡ ለዚህም ማሳያ በማቴ.19፥11-12 ላይ ባነሱት ጥያቄ ተነስቶ ሲመልስላቸው ይህ ለተሰጠው ነው
ለሁሉም የሚቻል አይደለም ከእናታቸው ማሕፀን እንዲሁ የተወለዱ ጃንደረቦች አሉ፣ሰዎች የሰለቡአቸውም ጃንደረቦች አሉ፣ስለመንግስተ
ሰማት ራሳቸውን ጃንደረቦች ያደረጉ አሉ፤መታገስ የሚችል ግን ይታገስ ይላል፡፡ ፡፡ብሕትውናም ኾነ ምንኵስና፣ በቅዱሳት መጻሕፍት
የተጠቀሰ፣ ከግላዊ አቋም የሚመጣ፣ ግዴታ የሌለበት፣ የኅሊና ውሳኔና ሕገ ፈቃድ ነው፡፡ በፈቃድ ወደው ከተቀበሉት በኋላ፣ ማጥበቅና
ማክበር ካልተቻለም ሕዝባውያን ኹኖ መኖር እንጅ፣ ቀደምት ቅዱሳን አበው (ፍትሐ ነገሥት አን. 10 ክፍል 7) (እንደ ነብዩ ኤልያስ
(2ኛነገሥ.2፥ 1 – 15፤ 4፥ 1 – 42፤ ማቴ.3፥1፤ ሉቃ.1፥1 – 5) ፣እንደ መልከፄዴቅ (ዘፍጥ.14፥ 17ዕብ.7፥ 1
– 14 ብዙ ቅድስና የሠሩበትን፤ በድንግልና በንጽሕና ተጠብቀው የክብር ክብር የወረሱበትን ሕገ ብሕትውና ወይም ሥርዓተ ምንኵስና፣
አኹን አንዳንዶች እንደሚያደርጉት፣ ዓርማውን አድርጎ ዓላማና ግብሩን ትቶ ማቃለልና ማጣጣል፤ እንዳልኾነ አድርጎ በመያዝ መታየትና
ተነቅፎ ማስነቀፍ የሚገባ አይደለም፡፡ ፤ ከኹሉ በፊት፦ ሀብትን ሽቶ ለድኾች መስጠትን አለመቻል፤ ከራሱ የመነጨ ፈቃድ የሌለውና
3 ወይም 6 ዓመት በአመክሮ አለማገልገል፤ የዚኽ ዓለም ሹመት ሽልማት መፈለግ ያለቀቀው ሰው መኾን፤ መጽሐፈ መነኰሳትን፣ ገድለ
ቅዱሳንን አንብቦ ያላወቀ፣ ሥርዓተ ምንኵስናን ያልጠነቀቀ ኹኖ መገኘት ለምንኵስና አያበቃም፡፡ (ፍትሐ ነገሥት አን. 10 ክፍል
1 እስከ 7)፡፡ ርእሰ መነኮሳት አባታችን አባ እንጦኒዎስና ርእሰ ባህታዊያን አባ ጳውሊ አንድ ወቅት ተገናነውተው መንፈስ ቅዱስ
የገለፀላቸውን ሲጨዋወቱ ለአባ እንጦንዮስ ክብሩ ምንኩስና ነበርና መልአኩ ሰርቶ ያመነኮሰበትን ቆብ አድርጎ አይቶታል ቅዱስ ጳውሊን
ይህችን ቆብ በኔ ብቻ የሚቀር እንደሆነ ለሌላም የሚያልፍ የሚተርፍ እንደሆነ አመልክትልኝ አለው፤ አባ ጳውሊም ወደ እግዚአብሄር አመለከተ(ፀለየ) ወዲያው ተገለጠለት ፤ወአክሞሰሰ ጳውሊ(ደስ
)አለው፤ ምን አየህ አለው፤ ነጫጭ ርግቦች በጠፈር ሞልተው አንተ እየመራሃቸው ተከትለውህ ሲሄዱ አየሁ አለው፡፡ ምንድነው ቢለው
እነዚህማ በቆብህ የምትወልዳቸው ንፁሀን ፃድቃን ልጆችህ ናቸው አለው፡፡ እስኪ ደግመህ ወደ እግዚአብሄር አመልክትልኝ አለው፤ ጳውሊም ደግሞ ፀለየ እግዚአብሄርም
ገለፀለት፣ ወደመነ ገፁ ለጳውሊ ይላል፣ የጳውሊ ፊቱ አዘነ ተከዘ፡፡ ምነው ቢለው ፀአዳ ሆነው ያየዋቸው እርግቦች ከክንፋቸው ላይ
ጥቁር ተቀላቅሎባቸው አየሁ አለው፡፡ ምንድነው ናቸው ቢለው ፅድቅና ሐጢአትን እየቀላቀሉ የሚሰሩ መነኮሳት ልጆችህ ናቸው አለው፡፡
ሶስተኛ አመልክትልኝ አለው ጳውሊም አመለከተ ገዐረ ወበከየ ለጳውሎስ ፣አባ ጳውሊ ድምፁን ከፍ አድርጎ ጮኸ፣ ምነው ምን ሆንክ አለው
አባ እንጦኒዎስ ጳውሎስን፤እርግብስ ናቸው ያየኋቸው ነገር ግን እንደ ቁራ ጠቁረው አየኋቸው አለው፡፡ ምንድናቸው ቢለው ››ኃሳስያነ ሹመት መፍቀርያነ ንዋይ እለ ይሰርዑ በነግህ
ማእደ መኳንንት ይላቸዋል፣እነዚህማ በፍፃሜ ዘመን የሚነሱ ሹመጽን ሽልማትን የሚፈልጉ ለገንዘብ የሚለፉ ገንዘብን የሚያፈቅሩ እንደመኳንንት
በጠዋት ተነስተው ማእድ አሰናድተው የላመ የጣመ የሚመገቡ የሞቀ የደመቀ ለብሰው ከተማ ለከተማ ቆብክን ደፍተው እዩኝ ሸልሙኝ ስገዱልኝ
የሚሉ ፣ አድናለሁ አጋንንትን እቀጠቅጣለሁ አወጣለሁ እያሉ የሚታበዪ ሀጥአን ልጆችህ ናቸው›› አለው፡፡(መፅሀፈ መነኮሳት መግቢያ)፡፡
ዛሬ ለቤተክርስቲያን ፈተና ከሆኑት መካከል እነዚህ መነኮሳት ናቸው እንደ አምልኮ ህዝብን ተከተሉኝ እያሉ በምትሀት ተአምራቸው ምንኩስናንም
የሚያስነቅፉ ምእመናንን የሚያውኩ ቤተክርስቲንን የሚያስነውሩ የዘመኑ ፈተናዎች የሆኑት፡፡ ይህም ለኛ በዘመናችን የተደቀነብን ፈተና
ነው ፡፡ እነዚህ
መነኮሳት ነን የሚሉ አጥማቂዎች ዋናው ዓላማቸው ምእመናንን ከበረታቸው አስኮብልሎ ወደነሱ ብቻ እንዲያዩና እነሱን ብቻ እንዲከተሉ በማድረግ ገንዘብ መሰብሰብ በመጨረሻም ለዲያብሎስ አሳልፎ መስጠት ነው፡፡ እነዚህ ሐሳውያን አጥማቂዎች፣ ተአምር ሠራን ብለው የሚያወሩ የሚያስወሩ በተንቀሳቃሽ ምስልም ድንቅ ነው ያሉትን ሥራቸውን ቀርጸው ራሳቸውን የሚያስተዋውቁ ቤተክርስትያንን ግን የሚንቁ ናቸው፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ተግባር ከየትኛው የቤተክርስቲያናችን ቅዱስ ያላየነውና ያልሰማነው እኩይ ተግባር ነው፡፡ በመሠረቱ ተአምር ማድረግ የሃይማኖተኝነት አልያም የጽድቅ መገለጫ አድርጎ መውሰድ የወፍጮ ድንጋይ ተሸክሞ ወደጥልቅ ባሕር እየወረዱ ከባሕሩ ለመውጣት የመፍጨርጨር ያህል ከባድ ነው፡፡ ሐዋርያትም ተከታዮቻቸውም ተአምራትን እንዳደረጉ ብናውቅም ጠንቋዮችና አስማተኞችም በዘመነ ሐዋርያት ተአምር ያደረጉ እንደነበር ተጽፎልናል፡፡ ሙሴ በፈርዖን ፊት በአሮን በትር ምክንያት ተአምር እንዳደረገ ሲጻፍልን ሙሴን የተቃወሙት ኢያኔስና ኢያንበሬስ በአስማታቸው ሙሴ ያደረገውን ተአምር እንዳደረጉ ሳይጻፍልን አልታለፈም፤ ምንም እንኳ የሙሴ እባብ የአስማተኞቹን እባብ ውጣ የእነሱን ከንቱነት ብታስረዳንም፡፡ ጌታችንም በመጨረሻው ዘመን ድንቃ ድንቅ ተአምራት በሐሳውያን መሲሓን እንደሚደረጉ ሲነግረን የድንቃ ድንቅነታቸውን መጠንም “የተመረጡት እንኳ እስኪያስቱ ድረስ” ብሎ ነው የገለጸው /ማቴ.24፥24/፡፡ ታድያ እነዚህን ሰዎች ቀርበን የቤተክርስትያን ትምህርት ተምረን ስንዴውን ከገለባው የምንለይበት መንሽ ካልያዝን የአባቶቻችንን ፈለግ ተከትለን ምግባራቸውን ካላወቅንባቸው እንዴት ልናውቃቸው እንችላለን? እነዚህን ሰዎች በየዋህነት የሚከተሉትን ምእመናንን ቀርበን ማዳን ካልቻልን፣ “ይሁንልን” ብለው ስሑት መንገዳቸውን ወደውና ፈቅደው የሚከተሉትን ሰዎችንስ አስተምረን መክረንና ገስጸን ከእቅፏ እንዳይሔዱ ማድረግ ከሁላችንም የሚጠበቅ ተግባር ሊሆን ይገባዋል፡፡
"ለክፉ ስራው ይጠበባል" ይላሉ
ብፁእ አባታችን አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ በረከታቸው ይደርብንና ጌታችንና መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብልህነቱን እንዲህ ብሎ ገልጧል
". እንደ እባብ ብልሆች " ማቴ 10:16: እባብ ዲያቢሎስ እንደ ኾነ የቀደመውን እባብ ዘንዶውን እርሱም ዲያቢሎስ
እና ሰይጣኑ የተባለውን........ተብሎ ከተነገረው ቃል መረዳትይቻላል። ራእ20:2 ።ይህ እባብ ነው አዳምንና ሄዋንን ለውድቀት
የዳረጋቸው ። ይህ ተንኮለኛና ብልህ ነው ሰዎችን ከእግዚአብሔር መንገድና ፈቃድ የሚያወጣበትን ለእያንዳንዱ ተስማሚ የኾነ ፈተናና
አመቺ ጊዜን ይፈልግለታል ። ለዚህ ድርጊቱ ተፈፃሚነትም የሰይጣን ማደሪያዎች ኒቆላዎስ በለአምና ኤልዛቤልን የክፍለ ዘመኑ አባ ዮሀንስ
ግርማና የነጀማነሺ ቡድን እህ ማርያም የተባሉ የሰይጣን ማደሪያዎችን አዘጋጅቶ እየሰራ ይገኛል ።ለዚህ ስራው መሳካትም ለዘመናት
የካበተ ልምድና እውቀት አለው ። ይህም ለሰባት ሺህ አመታት የሰውን ልጆች ሲዋጋ ኖሯል ። በእነዚህ ዘመናት ውስጥ የተለያዬ አስተሳሰብ
አመለካከት ጠባይ የኑሮ ኹኔታ ያላቸው ሰዎች ገጥመውታል። በመሆኑም ሰዎች መቸ በእምነታቸውና በምግባራቸው እንደሚፀኑ መቸ ቸልተኛ
እንደሚሆኑ በምን አይነት ፈተና እንደሚወድቁ ተረድቷል ።በማታለልናራሱን በመለወጥ በሐሰተኛነቱ ወደር የለሽ መሆኑ ይታወቃል ።ስለ
አላማው መሳካት ተግቶ ይሰራል ።እሚገርመው ደግሞ ሁሉንም ነገር ስለ አላማው ሲል ይታገሳል። እጂግ የሚገርመው ደግሞ እድገቶችንና
መሻሻሎችን ተከትሎ የሚሰራ መሆኑ ነው ። በዚህ በሳይንስ በረቀቀው አለም ውስጥ የመጨረሻዎቹን የሳይንስ መንገዶች ተከትሎ ይሰራል
። ለዚህ አላማ በመረጣቸው መሳሪያዎቹ ምእመናንን ከቤተክርስቲያን ከእምነታቸው ለመለያየትና ለማካካድ ተግቶ ይሰራል ። በተአምራትና
በምልክት ያሸበርቃል ። በአጥማቂዎችና በነቢያቶች (የነብዩ ኤልያስ ደቀመዛሙርት ነን ባዮች) ህዝብን ለሁለት ከፍሎታል ።፡ ይህም
ህዝቡ በምልክት የሚያምን ዘመናትን ተከትሎ በሚሰራው ተሐዋዋጭ ምልክት የሚያምን ህዝብ መሆኑን ተገነዘብን" ክፉና አመንዝራ
ትውልድ ምልክት ይሻል።"(ማቴ 16:4) ምልክትን መከተል የአመንዝራነት ምልክት ብቻ ሳይሆን አመንዝነት ነው ። "
የአመንዝራም ዓይን ድግዝግዝታን ይጠብቃል። "(ኢዮብ 24:15) እንደተባለ በአመንዝሮች ሰዎች ተስቦ መውደቅ ነው፡፡ እሚገርመው
የእነዚህ ተከታዮች ለእግዚአብሔር ክብር ሳይሰጡ ለአጥማቂዎቹ ክብር መስጠታቸው ነው፡፡ አጥማቂዎቹም እንደ አባታቸው እንደዳቢሎስ
ንግስናን ተከናንበዋል ። ተክለ ሃይማኖትን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስን ቅድሰት ኢየሉጣን ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስን ክርስቶስ ሰምራን
የማያውቅ ትውልድ አባ ግርማንና አባ ዮሐንስን ሌሎችንም ሲከተል ያሳዝናል፡፡ስለ ድንግል ማርያም ውዴሴ ማርያምን ማለት ያቃተው ትውልድ
ስለአጭበርባሪዎች ይከራከራል፡፡ የአምላክ እናት ስዕል ሳይኖረው ገና ምንም ያልሆኑ ያጭበርባሪዎችን ፎቶ ይዞ ይዞራል፡፡ "
ብዙዎችም በመዳራታቸው ይከተሉአቸዋል በእነርሱም ጠንቅ የእውነት መንገድ ይሰደባል።" (2ኛ የጴጥሮስ መልእክት 2:2) ተብሎ
እንደተጻፈ እያንዳዱ በእንድህ ይከተላል፡፡ ምልክትስ ለዮናስ ከተገለጠው ለነነዌ ሰዎች ከተደረገው ሌላ ምልክት አያስፈልግም እንዳለ
ጌታችን አስፈላጊ ቢሆን ኖሮ እግዚአብሔር በሰጠን ነበረ፡፡ ተአምራማድረግ የቤተክርስቲያን ቀዳሚ ስራ አይደለም ተአምር ብንል እንኳን
አምላክ ሰው ሆኖ በተዋህዶ ከመገኘቱ የተሻለም የበለጠም ተአምር የለም አይደረግምም ። ማንም አይሰራውም ። ድህነትስ ብንል አምላክ
ሰው ሆኖ ከፈፀመው የድህነት ስራ የበለጠ ተአምር የለም ከአምላክ በስተቀር ሊፈፅመው የሚችል ከአዳም ወገን ማንም የለም ብዙዎች
ተአምራትን አየን እያሉ በምትሐት በሐሠተኛ ነቢያት ተወስደዋል ብዙዎች በወንጌሉ ተሰናክለውበታል ። ከዚህ ከተነገሩት ምልክት የበለጠ
ምልክት የለም ። ሰዎች ከጌታ የበለጠ ተአምር አደረግን እያሉ ብዙዎችን ከመንገዳቸው አስተዋቸዋል ። ይህ የሰይጣን የካበተ ልምድ
ነው። ስለዚህ ትውልድ ሆይ ተመለስ ትውልድ ሆይ አስተውል ትውልድ ሆይ የምትከተለውን መርምር ። ብዙዎች በጌታህ ስም የቅዱሳኑን
ስም እየጠሩ ይመጣሉ እኛ ነን እያሉ ። መንፈስ ከወዴት እንደሆነ መርምር ሰዎችን ልታምናቸው አልተፈቀደልህም ይልቁንም ንስሀ ገብተህ
በስጋ ወደሙ ብትታተም ድህነትህእውን መንገድህ ቀና ይሆናል ። ነገር ግን በፈራሽ በስባሽ በሐሰተኛ ፈውስ በየጸበል ቤቱ ህዝቡ ሁሉ
ተመስጎ ሲጋፋ ታገኛለችሁ፡፡፡ ተጠንቀቁ ዘመናችሁ የከበደ እንደሆን አስተውሉ፣ ተዎዳጆች ሆይ ሰዎችን የሚአደርጉትን ምልክት አይቶ
መከተል የሚበላ ሣር እያዬ ገደል የሚገባ የተራበ በሬን ይመስላል፡፡አንዳንዶች ገና ለገና ምልክት ስላዩ ሰውየው ቅዱስ የሆነ ይመስላቸዋል፡፡ምልክት
ማሳየት(ምትሀት) ማድረግ የቅድስና ማረጋገጫ አይደለም፡፡ይልቁንም ለስህተት የሚዳርግ ይሆናል፡፡ እነዚህ ሐሰተኞች ሰዎች ውሸትን
ከልባቸው አንቅተው የሚናገሩ እራሳቸውን ከፍ ያደረጉ ሰዎች ናቸው፡፡ <<እራሳቸውን ጻድቅ ነኝ ቅዱስ ነኝ
>>ያሉ በታሪክ አንድም ኦርቶዶክሳዊ አባት ተነስቶ አያውቅም፡፡አባቶቻችን እነርሱ ዝቅ ጌታን ከፍ እያደረጉ ነው ያሳዩን፡፡
በዘመኔም ሆነ በታሪክ በግድላት የራሱን ተጋድሎ የጻፈ ፃድቅ አላየሁም፡፡ እራሴ አዳኝ ነኝ ጌታ መርጦኛል ብሎ ካልሰራው ካልፈወስኩ
ያለ ቅዱስ ወይም ካልነገስኩ ያለች ቅድስት የለችም ። ሰዎች ወዴት እየሄዱ ነው ነቢያት ዝቅ ዝቅ ብለው የተናገሩለትን አትርሱ እንጂ
" እኔ የጫማውን ጠፍር ልፈታ የማይገባኝ፥ ከእኔ በኋላ የሚመጣው # ከእኔ # ይልቅ # የሚከብር ይህ ነው አላቸው።"(ዮሐ
1:27) እያሉ እራሳቸውን ዝቅ ሲያደርጉ ክብርን ሁሉ ለእግዚአብሔር ሲሰጡ ነው የተማርንው፡፡ ቅዱሳን አባቶች የታመሙትን በስውር ከፈውሱ በኋላ ከዛ አካባቢ
ይጠፉ ነበር።እኔ አልበቃውም በምን አቅሜስ እፈውሳለው እያሉ በትህትና በመሆን ከንቱ ውዳሴን በመፍራት ይኖሩ ነበር። በርግጥ በዚህ
ዘመን እንዲህ ያሉ ሰዎችን እንዲህ ብየ በአውደ ምህረት ወይም በማንኛውም የማህበራዊ ሚዲያ ትክክል አይደሉም ብየ ለማስተማር አስበውና
እንደገና የራሴን ሀጢአት ባሰብኩት ጊዜ እጅግ ይከብደኝ እና አዝናለሁ፡፡ ቢሆንም ግን የቤተክርስቲያን ስርአት ሲጣስ ማየቴ ምእመናን
ከአምልኮ እግዚአብሄር ወደ አምልኮ ሰብእ ሲመለሱ ከስብሃተ እግዚአብሄር ወደ ስብሀተ ሰብእ ሲመለሱ የበለጠ ህሊናየ አምርሮ ይመንናል፣ቅንአተ
ቤተእግዚአብሄር አለብኝና ባላውቀው ባልማረው ቅሉ እንዲሁ ቤቱ ፍቅር ይዞኛልና አንደበቴን ዘግቸ እጀን አጣጥፌ መቀመጡ ይከብድብኛል፡፡
ታላላቆቻችንም ለትህትና ይሆን በቸልተኝነት ይህንን እያዩና እየሰሙ ዝምታን መርጠዋል፡፡ይህ እጂግ አስደማሚ ነው፡፡ የዚህ አይነት
አጥማቂዎችየመናፍሰት አሰራርን ተከትለው በሚሰሩ ሰዎች ውስጥ የምናገኛቸው ሲሆን በመፅሀፍ ቅዱስ እና በቅዱሳን አባቶቻችን ህወት
ሚዛን ስናያቸው፤
1.
ቅድስና
ወይም ጻጋ የሌለው ተአምር አድራጊ፡ በቅዱሳት መጻሕፍት
በገድል በድርሳናት ስለ ፈውስ ብዙ ተጠቅሷል። በክርስትና ውስጥ በተለየ የመንፈሳዊነት፤ የገዳማዊነት በተአምር አድራጊነት፤ የተመሰከረለት
ሕይወት ሳይኖረው በፈውስ የታውቀ ጻድቅ፤ ወይም ቅዱስ አልነበረም። አንድም ቦታ የለም። አንድም ቦታ ፈዋሽ ስለመሆናቸው ማስታወቂያ
አያስነግሩም፤ እኔ ፈወስኩ የሚሉ አባቶች የሉንም አልነበሩንም። ዛሬ ግን አለምን የሞላው ሰው ወደ ግለሰቦች አይኑን አዙሯል።
2.
ተአምር
የወንጌልን ትምሕርት ለማጽናት እንጂ መሰረታዊ ጉዳይ አይደለም። ተአምር ማድረግ የአንድ ሰው እውነተኛነትን
አያረጋግጥም። የፈርዖን ጠንቋዮች እንደ ሙሴ ሁሉ በትራቸውምን አባብ አድርገዋል። ተአምር እውነት ከሆነ ለምን አናምናቸውም? ዘጸ.
7:9 ። ሳኦል ወደ ጠንቋይዋ ሴት በመሔድ ሳሙኤልን አስነሺልኝ በማለት ይጠይቃታል። እርሷም ሳሙኤልን ጠርታ አስነስታ ለሳኦል አሳየችው
ይላል። ታድያ ጠንቋይ ልንከተል ነው?። 1ሳሙ.28:8 ተአምራትን እንደ እውነተኛነት ማሳያ ማየት ሞኝነት ነው። ጌታ ስለ ነጣቂ
ተኩላዎች ተግባር ሲያስተምር በግራ እንዲቆሙ የፈረደባቸው ሰዎች አኮ የሰጡት ምላሽ” በዚያ ቀን ብዙዎች፦ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥
በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን፥ በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን፥ በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን? ይሉኛል።” የሚል
ነው። ጌታ ግን አላውቃችሁም የሚል ምላሽ ነበር የሰጣቸው። እነዚህ ሰዎች አኮ ትንቢት ተናግረዋል፤ አጋንንት አውጥተዋል፤ ፈውሰዋል።
ግን እውነተኛነታቸውን አልተመሰከረላቸውም።
3.
መናፍስትን
ምስክር ማድረግ። በብዙ ምስል ወድምጽ(ቪዲዮ) ላይ እንደምናየው መናፍስቱን ስንት ናችሁ? እንማን ናችሁ፤ ማነው
የመተተብህ፤ምን ትሰሩ ነበር፡ ማን ታስደርጉት ነበር?...ወዘተ። እስቲ ይህንን ያደረገው ማን ነው? የሚል ጥያቄ ያቀርቡለታል እሱም
ይመልሳል። ቡዳ ነኝ እገሊት በላችኝ፤ እገሌ በላኝ ይላል። ይህንን ምስክር ተቀብሎ ሌላው በልቶኛል፤ በልታኛለች ባለው ላይ ቂም
ይይዛል።ጠቡ ይቀጥላል፡፤ ሰይጣን መቼ ነው የእውነት ምስክር የሆነው። “የሐሰት አባት” ተባለ እንጂ። ጌታችንም “አንተ እርኩስ
መንፈስ ውጣ” ነበር ያለው። ገድለ ጊዮርጊስን ገድለ ተከላ ሃይማኖትን እንመልከት “በጌታዬ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ውጣ” ነው ያለው
ቅዱስ ጊዮርጊስ። ሰይታንን ምስክርነት አልጠየቀውም።
4.
ዝና እና
እውቅና
።ዛሬ አጥማቂ ተብየዎቹ ዝናቸው በዓለም ናኝቷል። ይምጡልን በዝቷል። ቅዱሳን ገድላትን ስናነብ ግን ከዚህ በተገላቢጦሽ አናነባላን።
አባ ተክለ ሐይማኖት ጻድቁ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ማለትም ከጻድቁ አባ በጸሎተ ሚካኤል ገዳም ወደ ሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳም የሔዱት
በሚያደርጉት ተአምር ምክንያት ስማቸው ከፍ በማለቱ፤ ብዙ ሰዎች በመሰብሰባቸው ምክንያት ነው። መላከ መንክራት፤ ፋዋሴ ዱያን ርእሰ
ባህታዊያን እየተባሉ ስም እያስለጠፉ፤ መጻፍ እየጻፉ ሲዲ እየሸጡ ያኖራሉ። ሲዲ ለመግዛት እና የመናፍስትን ጫጫታ ለመስማት ብዙ
ብር ሲያወጡ፡ ገድል እና ድርሳን ገዝተው ለማንበብ ለመጸለይ ግን አይመጣላችውም። ምክንያቱም ሰው እና ተአምር ላይ እንጂ መሰረታዊው
ትምህርት ላይ ግድ የላቸውም።
5.
ባለ መናፍስቱ
የሥላሴን፤ የድንግል ማርያምን የመላእክቱን፤ ስም ሲጠራ ምንም ችግር የለበትም። ጥራ
ሲባል ይጠራል። አጥማቂውን ሰውዬ ግርማ ለማለት፤ ስም ለመጥራት ግን “እንቃጠላለን፡ ስምህን መጥራት አንችልም” ይላል፡፤ ከዚሕ
የሚከፋው ደግሞ አንዳንዴ የሥላሴን ፡ የኢየሱስ ክርስቶስን ስም ይጠራና የድንግል ማርያምን ስም አንጠራም እርሷ ታቃጥለናለች ይላል።
ሕዝቡ በእልልታ ይደግፋል። ይሕ ከቤተ ክርስቲያን ትምሕርት ጋር ይጣረሳል። የማን ክብር በልጦ ነው። የሥላሴ ወይስ የድንግል ማርያም።
ፈጣሪና ፍጡር። ሰይጣን ምን እያስተማረ እንዳለ እንኳን በውል ያስተዋልን አይመስለንም። በራስ መድረክ በሰይጣን ግብ ማስቆጠር ማለት
አይደል።
6.
የቅዱሳን
አባቶች ታሪክ የሚያስረዳን በጸሎት የተጠቀሙበት መስቀላቸው ልብሳቸው ጥላቸው ሲፈውስ አንብበናል። ቅድስናቸው
ለመቋሚያቸው፤ ለመቁጠሪያቸው ለልብሳቸው ሲተርፍ። ዛሬ የፈውሱ ምንጭ መቁጠሪያ ሆኖ መቁጠሪያ ሽያጭ ዋና የገቢ ምንጭ ሆኗል። “ቅብዓ
ቅዱስ” እየተባለ ከመርካቶ የተገዛ ዘይት ሲቸበቸብ እያየን ነው። መቁጠሪያ አእምሮ ሰብስቦ እየቆጠሩ ለመጸለይ በመቁጠር ኅሊና እንዳይበተን
ስግደትን ለመቀጠር ያገለግላል እንጂ ስሪቱ ለፈውስ የሚውል አይደለም።
7.
በነባር
ወይም በተፈጥሮ በፈለቀ ጠበል አለመጠቀም። አብዛኞቹ “አጥማቂያን” በአካባቢው አልያ በቤተ ክርስቲያን የፈለቀ
ጠበል ካለ በርሱ አያጠምቁም። በጥቅሉ እነዚህ አሰራራቸው ከመፅሀፍም ከቅዱሳን አበው የህይወት ክንውንም ከወንጌልም ከምንም የማይገጥም
የማይገናኝ ሂደትን እንደ ስርአት አድርጎ ምእመናንን ከእምነት ማባከን ነው፡፡
3. አጥማቅያን አጠቃላይ ባህርያቸውን
ስንመለከት
1. ከመሰረታዊው የቤተክርስቲያን አስተምኅሮ ጋር የሚጋጭ ትምህርትም ተግባርም አለባቸው።
2. ለእውነተኛነታቸው ማረጋገጫ የሚጠቅሙበት ተአምራት ማድረግ ነው።
3. የቤተ ክርስቲያን አባቶችን መንቀፍ ላይ አንድ አቋም አላቸው። መልካም ስላደረግን፤ ስለፈውስን ፤በለጡን ብለው
ቀኑብን፤ አሳደዱን፤ አገዱን በማለት ምሬታቸውን ወደ ቀናኢው ሕዝብ ያቀርባሉ። ቤተ ክህነቱ አገደን ምዕመናን ይህንን ተከትለው ይደናገራሉ።
4. የመንፈሳዊነት፤ የገዳም የቅድስና ታሪክ የላቸውም።
5. ታላቅ የገንዘብ ድጋፍ ያፈሩ ታላላቅ ፎቆች የገነቡ
6. “ባሕታውያን አጥማቂ” ነን ባዮች ሥልጣነ ክሕነት እንዴት እንዳመጡ አይታወቅም።
ለኔ ዛሬ እነዚህ ሰዎች በሚሊዮን
የሚቆጠሩ ተከታዮችን አፍርተው በየአጥቢያችን ያሉ ተከታዮች ጉባኤ ሲዘጋጅ አባዮሀንስ ካልመጣ ሌላ ሰባኪ መምህር መጥቶ ሊሰብከን
አንፈልግም ይላሉ፡፡ እንዲህ እስኪባል ድረስ ቤተክርስቲያን እየተቸገረች ነው፡፡ ዛሬ በዚህ ፅኁፍ ለማሳሰብ የወደድኩት በወንቅሸት
ገዳም ስለተከሰተውና እየሆነ ስላለው ሁኔታ አስመልክቶ ነው፡፡ ይህውም ስለ አባ ዮሀንስ ነው፡፡
1.
አባ ዮሀንስ
ማናቸው
የሚል ጥያቄ ስናነሳ ይህንን የምፅፈው ፈልጌ ካገኘውት መረጃ ተነስቸ ነው፡፡ ይህንም ስል ስለ አንዲት ቤክርስቲያን ስል እንጂ እሳቸውን
ለማወቅ የወሰደኝ ያስገደደኝ ስጋዊ ደማዊ አላማ አይደለም ፡፡ ስለምእመናን ስል ነውና፡፡ መጀመሪያ ከመግቢያየ ስለ ርእሰ ባህታዊያን
ቅዱስ አባ ጳውሊ እና ስለ ርእሰ መነኮሳት ቅዱስ አባ እንጦንዮስ አንስቸ ነበረ ፡፡ የእነሱን የምንኩስናና የብህትውና ህይወትና
የተነበዩትን ራእይ እያስታወስን እንተነትናለን ፡፡ አባቶቻችን የምናውቃችው በመንፈሳዊ ቅድስና ህወታቸው በተጋድሎአቸው ከሰው ተለይተው
ከአራዊት ጋር ተስማምተው ለምለም ከሌለበት ውሃ ከማይፈልቅበት በረሀ ቋጥኝ ገብተው ይገድማሉ ሰው እንኳቅድስናቸውን ሰምቶ ቢሄድ
ተደብቀው ሰለአምላክ ክብር ብለው ራሳቸውን አዋርደው ሸሽተው ቦታ ቀይረው ይሰደዳሉና ፡፡ ዛሬ ግን አዲስ ነገር መጣ ትንቢት ነውና
እኛስ የትንቢት መፈፀሚያ እንሆን ዘንድ ስለምን ተኝተን እንመለከታለን; አዲስ ነገርስ በአባ ዮሀንስ የመጣ ባይሆንም የእኛ እነሱን
መከተላችን ግን አዲስ ነገር ነውና፡፡ ለመሆኑ አባ ዮሀንስ ማን ነበሩ የሚለውን ስንጠይቅ እንዲህ ሚል ወሬ ተነገረን ወሬስ ብቻ
አይደለም ሰው ሁኖ የተወለደበት ያደገበት የተማረበት የደቆነበት የቀሰሰበት የመነኮሰበት ይታወቃልና፡፡ አባ ዮሐንስ ከ2000 ዓ.ም
ቀደም ብሎ ነበር ዝናውን የምንሰማው "የሥላሴ ባርያ የወንጌል ገበሬ የበርሃው መናኝ" እያለ በአውደምህረት በሲዲም
አሳትሞ እራሱን ሲክብ ትምህርቱን አቋርጦ ዓውደ ምሕረቱን ጩኸት በጩኸት ሲያደርገውና ማን ነው ያቃጠለህ ሲለው አንተ ነህ ያቃጠለኝ
እያለ አጋንንት ሲፎክርና ጤነኞች ሲቅበዘበዙ ሲጨነቁ እርሱ በሚያሰማራቸው አጋንንትን እየጠየቅ ሲጫወቱ እናያለን ። ልክ እንደወንድሙ
አባ ግርማ ። እኔ ለመጀመሪያ ጊዜ ያየሁት ግን በ2002አ.ም ዘጠኙ ተአምራት በወንቅሸት ገዳም የምትል ከኢየሩሳለም እስከ ወንቅሸት
ገዳም የሚል ፅሑፍ መሠል ያለበት መፅሐፍ ተመልክቻለሁ ውስጡን ትንሽ ማንበብ ሞክሬ ነበረ። እናም መፅሐፉ የሚያወራው እራሱ በደመና
ተጭኖ ከኢየሩሳሌም ኢትዮጵያ እንደሚመላለስ እንዲሁም በራእይ ቦታውን እንዳየው እና እንዲሰራው እንደታዘዘ ነው የሚናገረው፡፡ የትውልድ ሀገሩ ጉምዝ ሲሆን በልጅነቱ መጥቶ ያደገ ምዕራብ
ጎጃም አቸፈር ወረዳ ልሁድ ማርያም በምትባል ቀበሌ ነው፡፡ ከዛ በኋላ ወደ ሜጫ ወረዳ እዛው ምዕራብ ጎጃም ዑራ ኢየሱስ በሚባል
ገዳም ከአባ ገብረ ማርያም ጋር መኖር ይጀምራል። አባ ገብረ ማርያም የሚባሉት በኃይለ ሥላሴ ዘመን ሀገር ገዥ የነበሩ ክህነት የሌላቸው
ጻድቅ አባት ናቸው። እርሳቸውን የማይታዘዘን ጎረምሳ በመሆኑ ረግመውታል ይላሉ ።, አሁን ላሊበላ የሚመላለሱት ጻድቅ መነኩሴ አባ
ኪዳነማሪያም ጋር አብረው ነበሩም ይባላል ።እሳቸውን ለማናገር ስላልተቻለ ነው እንጂ ። አባ ዮሀንስ አልታዘዘም ጎረምሳ ሁኖ አልላክም
ስላላቸው "ገነት ትዘጋብህ፣ ሕዝብ ይስገድልህ፣ በመቃብርህ ሰው አይቁም" እያሉ ረግመውት ስለነበር በእለተ እረፍታቸው
ተጣልቶ ሸሽቶ አልነበረም። "የሳቸው ርግማንና ትንቢት ነው እንዲህ ያደረገው" ይላሉ። "አባ ገብረ ማርያም
ከሞቱ ከአንድ ወር በኋላ ዮሐንስ ተመልሶ ወደ ዑራ ኢየሱስ ካባ ደርቦ መቋሚያ ይዞ አርቴፍሻል ዊግ ፀጉር በራሱ አንጠልጥሎ መጣ።"
ዑራ ኢየሱስ ገዳምን የመሠረቱት በወጣትነታቸው ሙት ያስነሱት ጻዲቁ አባ ዮሐንስ ናቸው እናም በእሳቸው ስም የሱን ስም ለማግነን
አስቦ ነበር። ግን ማድረግ ስላልቻለ መዳረሻውን ወደ ደራ ወረዳ ወንቅ እሸት በርሀ አደረገ። እስካሁን ክህነት በዚህ ቦታ ተሰጠው
የሚል መረጃ የለም ። መነሻው የሱዳን ዕፅ ቢሆንም በሀገራችን ሠርጎ በመግባት መዳረሻ አዘጋጅቷል። ትክል ድንጋይ በሚባል አካባቢ
ጠንቋዮች አሉ እዛ አካባቢ ነው የሚያሰራው የሚል መረጃ አለ። አባ
ዮሐንስ ተብየው ይህን ዕፅ ጨብጦ የሕዝብ ማታለያ ብዙ ዘዴዎችን በአጭር ጊዜ በመማር ብቅ አለና አርባ ዓመት በርሃ ቆየሁ እያለ
ይደነፋ ጀመር[wT1] ።
እርሱ
ግን ሰላሳ አመት በረሐ መንኛለሁ ዮሀንስ ወልደ ነጎድጓ ያጠመቀው ጌታን ብቻ ነው እኔ ግን ብዙ ሰው አጥምቄአለሁ ። እያለ መስቀሉን
አሰርቶ ይሸጣል ። የአካባቢውን ሰው በምታትና እርስ በእርስ በማፋጀት ከእርስቱ እንዲሸሽ ብሎም እንዲሞት በማድረግ ይዞታውን አስፋፋ።
ማጥመቁን ጀመረና አጋንንትን በአጋንንት ስም እያወጣ እንዲሁም በትዕቢት ሚካኤል ገብርኤል እሠሩት እያለ ያለ አቅሙ እያዘዘ፣ በሣልስቱ
ተመልሶ እንዲታመም እያደረገ፣ ጤነኛውን ሽባ እያደረገ ቀጠለ። አጋንንቱን ዮሐንስ አቃጠለኝ ጸሎቱ በላኝ እንዲል አስደረገና እሱን
ማምለክ ተጀመረ። ፎቶውን ሥዕል አድኖ አስመስሎ አሳተመና ተዳሰሱበት እያለ በ50 ብር ቸብችቦ ደጎስ ያለ ብር አገኘበትና በትልልቅ
ከተሞች ሕንጻውን ገነባ። በስልክ ይፈውሳል በቀን ከኢትዮጰያ ወደ አወስትራሊያ ወደ ሌሎችም ሀገሮች ይሄዳል ጠባቂ ወታደር አለው
። ሽርሽር ይንቀሳቀሳል ። ከተሐድሶዎች ጋር በመሆን የቅራርቶ መዝሙር በማውጣት ለብር ተብሎ በየሰው በር እየዞረ ሲሸጥና ጆሯችን
ሲሰማ እኛም በሞባይል አድርገን ሰማነው ይገርማል። በሰፊውና ተንኮል የተሞላውን አስኬማ አንስታችሁም ጉንጉን የውጭ ዊጉን እንዲሁም
ቅቤ የማይለየውን ራሱን ተመልከቱ። ሁሌ ይቀባል በዚህ ምክንያት አንድ ቀን በስህተት ቤተ መቅደስ ገብቶ አያውቅም" ይባላል
። ቅዳሴ አይቀድስም ቁርባን አያውቅም። መቁጠሪያ በክንድ ተጠምጥሟል እንጅ አይጸለይበትም።ግእዝ ሲናገር የሰማው አለ? መጽሐፍ ቅዱስን
ግን ሸምዶታል። ይህም ምትሀት ነው ብዙ ጊዜም ፍርድ ቤት ቀርበዋል የቀረቡበትም ብዙ ዶሴ ተይዞባቸው እንደነበር ይነገራል፡፡ ቆሞስ
አባ ዮሐንስ፡- በዐውደ ምሕረቱ ላይ ስለ ራሳቸው ክብር ብቻ በመስበክ፣ራሳቸውን ማወደስ፤ ከእኔ በላይ ማንም የለ፤ በማለት ራሳቸውን
ያጋንናሉ፤ከያሬዳዊው የዜማ ሥርዓት የወጣ ዘፈን መሰል መዝሙር እስከ ሌሊቱ ሰባት ሰዓት ድረስ በማሰማት የከተማውን ሕዝብ ዕረፍት
ይነሳሉ፤“ከእኔ በላይ ማንም የለም” በማለት ስለ ራሳቸው ክብር በዐውደ ምሕረቱ ሲመሰክሩና ሲያጋንኑ ከዋሉ በኋላ፣ የጸሎተ ቅዳሴው
ሰዓት ሲደርስ፣ ቅዱስ ቊርባኑን እያቃለሉ እንደማይጠቅም በማስመሰል ወደ መኖሪያ ቤታቸው ይሔዳሉ፤ ከቅዳሴ ውጭ ተመልሰው በመምጣት
ዘፈን መሰል መዝሙራቸውን ይቀጥላሉ፤ ምንኵስና ይቅርና አመክሮ እንኳን የሌላቸውን በጌጣጌጥ ያሸበረቁ ዓለማውያን ቆነጃጅትን በማሰባሰብ
ሥርዓተ ገዳምን ያፋልሳሉ፤ “ከቅዱሳን እኔ እበልጣለኹ፤ ቅዱሳን ምን ሠርተዋል” በማለት ክብረ ቅዱሳንን እያቃለሉ አማኙን ሕዝብ
ያደናግራሉ፤
2. በቤተክርስቲያን ላይ ያደረሱት የስርአተ ቤተክርስቲያን ጥሰት ምንድነው;
1.
ቤተ ክርስቲያን የአንድነት ቤት ስትሆን ምዕመናንን በመከፋፈልና በመካከላቸው ግርግር በመፍጠር እንዲረበሹ ማድረግ
2.
የራሳቸውን ፎቶ እንደ ስእል
አድህኖ በማሰራት መሸጡ እና እርሱን እየተሳለማችሁ ትድናላችሁ እያለ ማስተማሩ እና ፎቶውን በትልቅ ባነር አሰርቶ ከቤተክርስቲያኑ
መግቢያ ላይ በመለጠፍ እንዲሳለሙት ማድረጉ፡፡
3. በስርዓተ ቅዳሴ ጊዜ ቅዳሴን
ማቃለል ስርአቱን አለማክበር ረግጦ በመግባት ለምዕመናን መጥፎ አርዓያ በመሆን ምእመናንን ማሰናከል
4.
ራሱን እንደ መልዓክ በመቁጠር ስርዓተ ቤተ ክርስቲያንን በመዳፈር ከተሰራው ስርዓት ውጪ ሌላ ስርዓት በመፍጠር ለምሳሌ የፈውስ ጊዜ ብሎ ቅድስት ቤተክርስቲያን ዘወትር የምህረት የድህነት በር ስትሆን
አባ ዮሐንስ ግን የፈውስ ቀን እያሉ የሚያስተምሩት ከስርዓተ ቤተክርስቲያን ውጭ
የሆነ ስርአት መስራት
5.
ክርስቶስ ሰውን ለማዳን መከራ የተቀበለበት መስቀሉ የከበረ ሆኖ ሳለ
በማቃለል
የራሱን ስም ዮሀንስ ብሎ በላዩ በማስቀረጽ ለንግድ ማዋል
6.
ከቤተ ክርስቲያኗ የገንዘብ አስተዳደር ስርዓት ቃል አዋዲ ውጪ ሐብትና
ንብረት
በማባከን ለግልና ለግብር አበሮች መበልጸጊያ በማድረጉ በስሙ ቅዱስ አባ ዮሀንስ በሚል የንግድ ፈቃድ በማውጣት ያልተገባ ምንኩስናን
የሚያስነቅፍ ብሎም ቤተክርስቲንን የሚስነውር ነገር መስራቱ
7.
4. ቅዱስ ጊዮርጊስ 7ዓመት ተጋደለ እኔ ግን 30 ዓመት ተጋድያለሁ ብለው
ያስተማሩት ስርአተ ቤተክርስቲያን ያልጠበቀ እና የሰማእታትን
ፅኑ ተጋድሎ የሚያስነውር ስራ የሚሰሩ በመሆናቸው
8.
መስከረም1 ቀን የአባ ዮሐንስ በአለ ልደት ተብሎ እየታረደ የሚደገሰው ድግስ ለእሳቸው በመሆኑ እና ይህ ደግሞ በቤተክርስቲን
ስርአት አግባብ ባለመሆኑ እነውዲሁም እርሳቸው መነኮስ ሲሆኑ አለም በቃኝ ብለው ከሁከት ከጫጫታ ርቀው ንፅህ ጠብቀው የላመ የጣመ
ከመብላት ተቆጥበው በገዳም መኖርና ለፀሎት መትጋት ሲገባቸው እኒዲህ አይነት የአለም ጫጫታ በገዳሙ እንዲፈፀም በማድረጋቸው እና
ሌሎችም ምንኩስናን ክርስትናን የሚስነቅፉ የአህዛብ ስራ የሚሰሩ በመሆናቸው ሊነቀፉና በአባቶች አስተምህሮ ሊወገዙ ሚገባቸው ሰው
መሆናቸውን ልብ ልንል ገባል፡፡
3. የወረዳው ቤተክህነት ስለዚህ ሰው ምን ብለው ይሆን;
ገዳሙን እያስተዳደርኩት ነው የሚሉት ርእሰ ባህታዊያን ቆሞስ አባ ቅዱስ ዮሐንስ የሚያካሄደው
ድርጊት ከቤተክርስቲያን አስተምህሮ ውጭ በመሆኑ ለሀገረ ስብከቱ በፃፈው ደብዳቤ እንዳስታወቀው አስተዳዳሪው በገዳሙ በልማት ስም
የሚያደርገው እንቅስቃሴ እንዲሁም አስተምህሮ ከቤተክረስቲያን ውጭ መሆኑን እንዲሁም በዚህ አስተምህሮው የዋሀን ምእመናንን ከክርስትናቸው
እንዲሰናከሉ እና እንዲሁም ለከፋ ጉዳት እንደሚዳረጉ ተመልክተናል፡፡ እንዲሁም በወረዳው ቤተክህነት በሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ ፀሎትና
ቡራኬ ተከፍቶ ለሁለት ቀናት እንዲካሄድ አባታዊ መመሪያ ተሰጥቶበት የተዘጋጀውን አመታዊ የህዝብ ጉባኤ ሁከት በመፍጠር እና ጉባኤውን
እንዲቋረጥ በማድረግ ወንጌል እንዳይሰበክ እንዲሁም የተላከውን መምህር እስከማስደብደብ የደረሰ ፀያፍ ስራ በመስራት አስተዳደሩን
በማወክ ከአቅሙ በላይ መሆኑን በ28/09/2009 በቁጥር 378/09 በተፃፈ ደብዳቤ ለሀገረ ስብከቱ አሳውቋል፡፡ በዚህም መሰረት
የደራ ወረዳ ቤተ ክህነት፣ ለሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት እንዳስታወቀው፣ ራሱን “ርእሰ ባሕታውያን” ብሎ በሠየመው በዚኹ ግለሰብ ሁከት
የተነሣ፣ ሊቀ ካህናቱ የወረዳውን አብያተ ክርስቲያናት ለማዘዝና ለመምራት፤ ሊቃውንቱም ለማገልገልና ለማስተማር ተቸግረዋል፤ ሕዝቡም
እየተደናገረ ወደ ሌላ እምነት እስከ መፍለስ በመድረሱ፣ ግለሰቡ ከማንኛውም እንቅስቃሴ ታግዶ ማጣራት እንዲካሔድበትና ተገቢው ርምጃ
እንዲወሰድበት ጠይቋል


የሀገረ
ስብከቱ አስተዳደር ስለዚህ ሰው ምን አስተዳደራዊ ውሳኔ አሳለፈ;
የሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት የቤተ ክርስቲያኒቱን መተዳደርያ ደንብ/ቃለ ዐዋዲ/፣ ሥርዓተ ገዳምንና
ሥርዓተ ምንኵስናን በመጣስና በማፋለስ ሊቃውንቱን እያስቸገሩና ሕዝቡን እያደናገሩ ራሳቸውን “ርእሰ ባሕታውያን” ፣ “የወንጌል ገበሬ”
፣ “የበረሓው መናኝ” ፣ “የሥላሴ ባሪያ” እያሉ ሲጠሩ የሚታዩበትና የሚሰሙበት የቪዲዮ ምስልም ያላቸው “መልክእም የተደረሰላቸው”
፣ክላሽን ጨምሮ የጦር መሣሪያ የሚይዙ የግል ጠባቂዎች እንዳሏቸውና “መነኵሴውን ይቃወማሉ” በሚሏቸው ምእመናን ላይ በፈጸሙት ድብደባ
ተከሠው በደብረ ታቦር ፍርድ ቤት ቀርበው እንደነበር እንዲሁም በባሕር ዳር ከተማ ዘመናዊ ቤትና በአንበሳሜ ከተማ፣ ለወንቅእሸት
ገዳም ልማት፣ አስተዳደሩ በሰጠው መሬት ላይ፣ ካናዳ በምትኖር ግለሰብ ስም የሚገነባ ሕንፃ እየሰሩ ነው በተባሉት መነኵሴ ተጽዕኖ
ውስጥ ያሉትን ገዳማትና ሌሎች የወረዳውን አድባራት ለማስተዳደር ከአቅሙ በላይ እንደኾነበት፣ ወረዳ ቤተ ክህነቱ፣ ለሀገረ ስብከቱ
በጻፈው ደብዳቤ መግለፁን ተከትሎ በመጀመሪያወ ዙር በታህሳስ 23/2011 የማጣራት ስራ እስከ ጥር ወር እንዲሰራ ከዚህ በታች በተመለከተው
ደብዳቤ ችግሮችን በዝርዝር በማንሳት ትእዛዝ ማስተላለፉ ይታወሳል፡፡



ሀገረ ስብከቱ ከላይ ያለውን
የማጣራት ሂደት ካጠናቀቀ በኋላ በተነሱት ጉዳዮች ላይ በአፅንኦት በመመልከት የገዳሙ አስተዳደር የተሰጣቸውን መመሪያ ባለመቀበላቸው
ከዛም አልፎ በሀገረ ስብከቱ ላይ ዛቻና ማስፈራሪያ በማድረሳቸው የሀገረ ስብከቱ አስተዳደር ለቤተክርስቲያን እና ለምእመናን ይበጃል
ያለውን ውሳኔ ህገ ቤተክርስቲያንን ተከትሎ በህግ እንዲጣራ ውሳኔ ያስተላለፈ ሲሆን የውሳኔው ሀሳብ ከዚህ በታች በተያያዘው ድብዳቤ
ተመልክቷል፡፡
የውሳኔው ሀሳብ ባጭሩ
እንደሚከተለው ነው፡፡
1. በአባ ዮሐንስ ስም
የተቀረፀው መስቀል እንዳይሸጥ እና እንዲጣራልን
2. በ50 ብር የሚሸጠው
የአባ ዮሐንስ ፎቶ እንዳይሸጥ
3. በአንድነት ገዳሙ
የማይመለከታቸው ግለሰቦች ከገዳሙ እንዲወጡ
ካልሆነም በገዳሙ ስርዓት
መሠረት እንዲተዳደሩ
4. ቅዱስ ጊዮርጊስ
7ዓመት ተጋደለ እኔ ግን30 ዓመት ተጋድያለሁ ብለው
ያስተማሩት ስርአተ ቤተክርስቲያን
ያልጠበቀ ስለሆነ እንዲስተካከል
5. ከቤተክርስቲያኗ በር
ላይ ያለው የአባ ዮሐንስ ፎቶ በአስቸኳይ እንዲነሳ
6. መስከረም1 ቀን የአባ
ዮሐንስ ተስፋ ማርያም በአለ ልደት ተብሎ እየታረደ የሚደገሰው ድግስ እንዲቆም
8. ቅድስት ቤተክርስቲያን
ዘወትር የምህረት የድህነት በር ስትሆን አባ ዮሐንስ ግን የፈውስ ቀን እያሉ የሚያስተምሩት ከስርዓተ ቤተክርስቲያን ውጭ ስለሆነ
እንዳይካሄድ
9. በገዳሙ ስምተከፍቶ
የሚንቀሳቀሰው ሂሳብ ተመርምሮ እንዲታወቅ እና በቀጣይ የሀገረ ስብከቱ በሚሰጠው ውክልና መሠረት ሂሳቡ እንዲንቀሳቀስ
10. የገዳሙ መተዳደሪያ
ደንብ እንዲወጣለት ደንቡ ተሰርቶ ለሀገረ ስብከቱ ቀርቦ አስመርምረው የሚስተካከል ካለ ተስተካክሎ እንዲሰራ እንዲደረግ የሚል የውሳኔ
ሀሳብ ሲሰጥ የተጠቀሱትን ችግሮች በአስቸኳይ እንዲያስተካክሉ በያስተካከል ግን ሀ/ስብከቱ አስተዳደራዊ እርሞጃ የሚወስድ መሆኑ በተለይ
በሰ/ጎንደር በመተማ ወረዳ ኮኪት በሚባል አካባቢ በ2004ዓም በሰሊጥ ንግድ በኢንቨስትመንት ንግድ ፍቃድ መዝ. ቁጥር001377/6072
አባ ቅዱስ ዮሐንስ ተስፋማርያም በሚል በተመዘገበ ፍቃድ ካፒታል 10,90,000.00 ንግድ እየነገዱ መሆኑ የሚያሳዝን ድርጊት መሆኑን
አስተዳደር ጉባኤው ተመልክቶታል፡፡ ሌሎችም ከደብዳቤው ላይ ተመልከቱ



6. ከምእመናን ምን ይጠበቃል
ስለዚህ ጉዳይ መጽሐፍ ግን ምን ይላል??
ኢየሱስ ከፈወሰው በኀላ " እርሱም ለማንም
እንዳይናገር አዘዘው፥ ነገር ግን። ሄደህ ራስህን ለካህን አስመርምር ለእነርሱም ምስክር እንዲሆን ስለ መንጻትህ ሙሴ እንዳዘዘ መሥዋዕት
አቅርብ አለው።"(የሉቃ 5:14)፡፡ የእነዚህ አጥማቂዎች በመፅሀፍ ሲለካ በተቃራኒው ነው የምናገኘው፣ ጌታችንም እንዲህ
በሉ ብሎ አላስተማረም ሙሴ እንኳን እኔ አፈኮልታፋ ነኝ አፈዲዳ ነኝ እስራኤልን ከግብፅ ምድር አላወጣም አንተ ባለሟልክን ፈልግ
ሲለው እንመለከታለን፡፡ አባቶቻችን እንዲህ እናደርጋለን የማይሉት አስተማሪያቸው ጌታቸው ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲህ
አድርጎ አላስተማራቸውምና ነው፡፡ ተአምር ማድረግ የቤተክርስቲያኒቱ ዋና አላማ አይደለምና ምክንያቱም ተአምር በቤተክርስቲያናችን
ከጌታችን ከመድሀኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ሰው መሆን ወይም አምላክ ሰው ሆነ ሰው አምላክ ሆነ በተዋህዶ ከበረ ከሚለው የተሻለ
ተአምር የለም ይህንን ተአምር የሚያደርገውም ሰው ማንም ቅዱስ የሆነ ቢሆን ይህን ማድረግ ከቶ አይቻለውም " ድውይ ከፈወሰ
በኋላ እንኳን ለማንም አትናገር ብሎ ወደ ቤቱም ሰደደውና። ወደ መንደሩ አትግባ በመንደሩም ለማንም አንዳች አትናገር አለው።"(ማር
8:26) ይላል፡፡ ይህን ያደረገው ራሱ ባለቤቱ ነው እርሱ ሁሉን የሚችል አምላክ ሆኖ ሳለ ራሱን ይደብቃል ይህን ለደቀመዛሙርቱ
እንዲህ እያስተማራቸው ነው መምህረ ህግ ሰራኤ ህግ ነውና፡፡ አባቶቻችን እንኳእንዲህ አይነት በራሳቸው ተአብዮ አድርገው አያውቁም
መፈወስ እየቻሉ እንደማይችሉ ሆነው ይተውታል ለጌታቸው ክብር ይሰጣሉና፡፡ አጋንንት እራሳቸው ይመሰክራሉ" እርሱም የናዝሬቱ
ኢየሱስ ሆይ፥ ከአንተ ጋር ምን አለን? ልታጠፋን መጣህን? ማን እንደ ሆንህ አውቄአለሁ፥ የእግዚአብሔር ቅዱሱ ብሎ ጮኸ። ኢየሱስም።
ዝም በል ከእርሱም ውጣ ብሎ ገሠጸው።"(ማር 1:25)" የናዝሬቱ ኢየሱስ ሆይ፥ ከአንተ ጋር ምን አለን? ልታጠፋን
መጣህን? ማን እንደ ሆንህ አውቄሃለሁ፥ አንተ የእግዚአብሔር ቅዱሱ አለ።ኢየሱስም። ዝም በል ከእርሱም ውጣ ብሎ ገሠጸው። ጋኔኑም
በመካከላቸው ጥሎት ሳይጐዳው ከእርሱ ወጣ።"(የሉቃ 4:35) ምእመናትና ምእመናን ሆይ የዘመነኞቹ ፈዋሾች ከየት አግንተውት
ነው ታዲያ ሰብስበው ሲአንጫጩት የሚውሉት??? በትክክልም ሥራው የመንፈስ ቅዱስ እንዳልሆነ ግልጽ ነው፡
ማስረጃ
የእግዚአብሔር ጸጋ ተከፍሎ አይሰጥም፦"እግዚአብሔር
መንፈሱን ሰፍሮ አይሰጥም።"(ዮሐ 3:34) እነዚህ ሰዎች ግን ትንሾችን ሲአድኑ ብዙውን አያድኗቸውም ደጅ ጥና በሌላ ቀን
ና ይላሉ፡፡ ጸጋው ካላቸው ለምን ሁሉንም አያድኑም??? ስለእውነተኞቹ የሐዋርያት ፈውስ መጽሐፍ <<" ደግሞም
በኢየሩሳሌም ዙሪያ ካለችው ከተማ ድውያንንና በርኵሳን መናፍስት የተሰቃዩትን እያመጡ ብዙ ሰዎች ይሰበስቡ ነበር፤ ሁሉም ይፈወሱ
ነበር።>>"(የሐዋሥ5:16) ይላል እንጅ አንዳዶቹ ይድኑ ነበር አይልም፡፡
➋ አብዛኛዎቹ ታሠርናል አባ ዮሀንስ አስሮኛል ሲሉ ይሰማሉ ለመሆኑ
እንድህ አይነት ፈውስ አለን? ይህ አጋንቱን ከሰውየው ጋር ማስማማት ማለት ነው የእግዚአብሄር ፀጋ መንፈስ
ቅዱስ ባለበት እንዲህ አይደለም በፀበልም እንኳን ሲድኑ እንዲህ አይሉምና ነው፡፡
➌ድነናል የሚሉ ሰዎች ተመልሰው በዚያው
በሽታ መያዛቸው የተለየ ለውጥ አለመታየቱ፡፡ ይህ ደግሞ የእግዚአብሄርን
መንፈስ ፍፁም አይደልም የሚያስብል ነው፡፡ ሎቱ ስብሀት የእግዚአብሄር መንፈስስ ፍፁምነው እንዲህ ያለው መንፈስ ግን የአጋንንት
መንፈስ እንጂ፡፡ እግዚአብሄር በእምነት የለመኑትን የሚሰጥ አምላክ ነው እርሱም ፍጹም ነው ሰማይና ምድር ያልፋሉ ቃሌ ግን አያልፍም
እንዳለ ወንጌል፡፡
➍ እንፈውሳለን የሚሉት ሰዎች የራሳቸውን ክብር ፈላጊዎች መሆናቸው፡፡
ፈዋሾቹ ፎቶየንና መቁጠሪያየን ገዝታችሁ ቤታችሁ ውሰዱ ብለው ያዛሉ፡፡ እሚገርመው የክርስቶስን ሥጋና ደም ተቀበሉ አለማለታቸው ነው፡፡ፎቶ
ያድን ምእመናን ይህንን አስተውለው ሊገነዘቡትና ለመዝኑት ገባል፡፡ በቤተክርስቲያን እንዲህ ያለው አስተምህሮ ታይቶ ተሰምቶ አይታወቅም
በየትኛውም፡፡ በርግጥ ሀዋርያት ጥላቸው ሳይቀር እንደሚፈውስ ወንጌል ይናገራል ፡፡ ያን ደግሞ ሀዋርያት እንትኔ ያድናል እያሉ ሳይሆን
እኛ አንችልም የናዝሬቱ ኢየሱስ ያድንህ ብለው ትተውት ይሄዳሉ እንጂ አድንሀለው አውቅልሀሉ አላሉምና እነርሱም ጌታ እንደሚያድነው
ያውቃሉና እነርሱ ከሚጨነቁት በላይ የፈጠረው አምላክ አብዝቶ እንደሚጨነቅ ያውቃሉና፡፡ አጋንትን ማውጣትም ሆነ ማስወጣት ብርቅ አይደለም " ነገር ግን መናፍስት
ስለ ተገዙላችሁ በዚህ ደስ አይበላችሁ፥ ስማችሁ ግን በሰማያት ሰለ ተጻፈ ደስ ይበላችሁ።"(ሉቃ10:20) ተበሎ እንደተጻፈ
ነው፡፡ በዚህ ዘመን ብዙ ምእመናን ተአምርና ምልክት እየተከተሉ እየጠፉ ነው፣ በመሰረቱ ክርስቲያን ምልክትን አይቶ የሚከተል ሳይሆን
ምልክቱ የሚከተለው ነው፡፡ጌታም "ምልክት ይከተላችኀል "አለን እንጂ "ተከትላችሁ ሂዱ" አላለም፡፡
" ያመኑትንም እነዚህ ምልክቶች ይከተሉአቸዋል፤ በስሜ አጋንንትን ያወጣሉ፤ በአዲስ ቋንቋ ይናገራሉ፤ እባቦችን ይይዛሉ፥"(ማር16:17)
እንዳለ፡፡ በዚህ ዘመን ኃጢአቴ በዝቶ ታየኝ የሚል የለም እንጂ ጌታ ታየኝ ማርያም ተገለጠችልኝ የሚል ባለራእይ በዝቷል፡፡ "
እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ። ነቢያቱ ውሸት በስሜ ትንቢት ይናገራሉ፤ አላክኋቸውም፥ አላዘዝኋቸውም፥ አልተናገርኋቸውም፤ የውሸቱን
ራእይ ምዋርትንም ከንቱንም ነገር የልባቸውንም ሽንገላ ይሰብኩላችኋል። "(ኤር14:14) እንዳለ ጌታ ሳይላኩ ተልከናል የሚሉ
ሀሰተኞች አፍቃሬ ንዋይ በዝተዋልና ልንጠነቀቅ ይገባል፡፡ <<ሐሰተኛ ወሬ አትቀበል፤ ሐሰተኛ ምስክርም ትሆን ዘንድ ከኃጢአተኛ
ጋር እጅህን አታንሣ። ክፉውን ለማድረግ ብዙ ሰዎችን አትከተል፤ ፍርድንም
ለማጣመም ከብዙ ሰዎች ጋር ተስማምተህ አትመስክር።>> " ወዳጆች ሆይ፥ መንፈስን ሁሉ አትመኑ፥ ነገር ግን መናፍስት
ከእግዚአብሔር ሆነው እንደ ሆነ መርምሩ፤ ብዙዎች ሐሰተኞች ነቢያት ወደ ዓለም ወጥተዋልና።" (1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4:1)
፡፡ የነገረ ሃይማኖት ትምህርት እንዳይሰጥ ምእመናን ሃይማኖታቸውን በሚገባ እንዳያውቁ ያደናግራሉ፡፡ በዘመናችን ይህ ሊሆን ግድ እንደሆነ ሐዋርያው ቅዱስ ጰየጥሮስ በትንቢት መነጸርነት መልዕክቱ እንዲህ ሲል አስቀምጦልናል፤“ነገር ግን ሀሰተኞች ነቢያት በህዝቡም መካከል ነበሩ እንዲሁም በመካላችሁ ደግሞ ሐሰተኞች አስተማሪዎች ይሆናሉ ፤ እነርሱም የዋጃቸውን ጌታ እንኳን ክደው የሚፈጥንን ጥፋት በራሳቸው ላይ እየሳቡ የሚያጠፋ ኑፋቄን አሾልከው ያስገባሉ ብዙዎችም በመዳራታቸው ይከተሉዋቸዋል በእነርሱም ጠንቅ የእውነት መንገድ ይሰደባል፡፡ /2ኛ ጴጥሮስ፡ 2፥1-2/፡፡ ታዲያ በዘመናችን እየሆነው ያለው ጉዳይ ምን ያህል ተራርቆ ይሆን? ዓለምን የሚያሸንፈው እምነታችን ነው፡፡ የእምነታችንን ጽናት በማጠንከር ከመጣው ማንኛውም ዓይነት ፈተናን እናልፋለን፡፡ ይህንንም ለማድረግ በጾምና በጸሎት ልንበረታ ያስፈልገናል፡፡ ጌታችን በወንጌል ሲያስተምር ‹‹እስክመጣ ድረስ ያልኳችሁን ጠብቁ የሚል ትእዛዝ እንዳስተላለፈልን በትንቢት የተነገረው ይፈጸመን ዘንድ ግድ ነውና አባቶቻን ባስተማሩን ትምህርት ጸንተን ልንኖር ያስፈልጋል፡፡
……………………..ይቀጥላል
ያልተቋጨ
ነው፡፡
