ዓርብ 9 ሴፕቴምበር 2016

ሼር በማድረግዎ እናመሰግናለን
ይድረስ- ለእመቤታችን ወዳጆች
-ለመላው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ
-ከባህር ማዶም በስደት ሳላችሁ እመቤታችንን የተከተለቻችሁ የእግዚአብሔር ልጆች በሙሉ
-ለበጎ አድራጎት ማህበራት


፠፠፠በውኑ ቤቴ ፈርሶ ሳለ እናንተ በተሸለሙ ቤቶቻሁ ለመኖር ጊዜዉ ነውን( ትንቢተ ሐጌ 1፣4
፠ባይተዋር ማርያም፠✍✍

በደቡብ ወሎ ዞን ወግዲ ወረዳ ልዩ ስሙ አባርጋ በሚባለው ጎጥ ትገኛለች፡፡ ይህች ቤተክርስቲያን በአድስ መልክ የተመሰረተችው በ2007 አ.ም ነው፡፡ በቦታው ሚገኙት ምእመናን ቁትራቸው 60 የሚያህሉ ናቸው፡፡ ይህቸ ቦታ ቅድመ ታሪክ አላት ፤ እንዲህ ነበረ ይላሉ በቦታው የተገኙት እድሜ ጠገብ ሽማግሌዎች፣ እንድሚታወቀው 15ኛው መቶ ክ/ዘመን ለኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የጨለማ ዘመን ነበረ፣ ግራኝ አህመድ ከሰለባቸው ቦታዎች አንዱና በቀዳሚ የሚጠቀሰው የ ወግዲ ወረዳ ነው፡፡ በዚያም ዘመን በወግዲና በከላላ ወረዳ 44 ፍልፍል አብያተ ክርስቲያናት የሚገኙ ሲሆን ከነዚህም መካከል ዛሬ ተከፍተው እያገገሙ ያሉት 5 ፍልፍል ገዳማት ብቻ ሲሆኑ እነሱም፡ የአባጊዮርጊስ ዘጋስጫ እና አባ በፀሎተ ሚካኤል አንድነት ገዳም; የአባታችን አባ ፅጌ ድንግል ገዳም; የአባ ያእቆብ ገዳም; ገዛዛ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳምና የአቡነ እንድርያስ ገዳም ናቸው፡፡ ሌሎቹ ጊዜአቸውን እየጠበቁ በትንቢቱ መሰረት ይከፈታሉ ይላሉ እነዚህ ቀደምት አበው፡፡ ከፍልፍል አብያተ ክርስቲያናቱ ውጪ በአጥቢነት ይተዳደሩ የነበሩት ደብራት በግራኝ የተቃጠሉት ግን ብዙ ከመሆናቸው የተነሳ ቁጥራቸው በዉል አይታወቅም ይላሉ፡፡ ከነዚህም መካከል ይህች ቤተክርስቲያን የተተከለችባት አንዷ ስትሆን የቀድሞ ስሟ አፍቅራ ማርያም ትባል ነበር ይላሉ፡፡ ይህች የእመቤታችን ታቦት በግራኝ ተቃጥላ ቦታው ጫካ ሆኖ ከቆየ እነሆ ድፍን 481 አ.ም አስቆጠረ፡፡ አካባቢውንም ከሌላ ቦታ በመጡ ሙስሊሞች ተይዞ በተለይም ከነገሌ ቦረና እንደመጡ የሚነገርላቸው ህዝቦች በቀድሞ አጠራሩ የሳይንት ክፍለ ሀገር ሲሆን ዛሬ ግን ቦረና ሳይንት እየተባለ ከነገሌ ቦረና በመጡት ሰወች ስም ይጠራል፡፡ የወረዳውም ስም ከኦሮምኛ የተወሰደ እንደሆነ ይናገራሉ ከነዚህም ከመጡት የኦሮሞ ህዝቦች አብዛኛው በአጼ ዮሀንስ ዘመን እንደተጠመቁም ይናገራሉ፡፡ ቦታው ላይ እንዳየነው ግራኝ አህመድ አምጥቶ ያሰፈራቸው ህዝቦች ከተቃጠለችው ቤተክርስቲያን ቦታ ላይ ለብዙ ዘመናት ቤት ሰርተዉ እንደኖሩበትም ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ፡፡ ዛሬ ግን ይህ ቦታ (የነ አባ ፅጌ ድንግል አገር ፣ የነ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ አገር የነ አቡነ እንድርያስ ሀገር የነ አቡነ ያእቆብ አገር) ጊዜው ደርሶ በቦታው የእመቤታችን ፅላት ተተክሎበታል፡፡ እጅግ ደስ ያሰኛል ፡፡ ነገር ግን በቦታው ታቦቲቱን የተከላት አንድ ቄስ ብቻ ነው ያለው ይህ ቄስ የ60 ምእመናን አባታቸው ነው ሌላ ቄስም ሆነ ዲያቆን የላቸውም በቦታው ላይ ለታቦቲቱ ማረፊ የተሰራችው ጎጆ ከታች እንደምተመለከቱት ኩሽና ቤት እንኳን አታክልም፡፡ ወግዲ ወረዳ በ2007 አም በተነሰሳው የኢሊኖ ድርቅ ተፅእኖ ከወደቁት ወረዳዎች አንዱ ሲሆን መእመናኑ ከድህነታቸው አኳያ ቅዳሴ ቤቷን መስራት አልቻሉም፡፡ ከዛ በፊት ምእመኑ የ1፡30 ሰአት መንገድ እየሄዱ ይገለገሉ እንደነበር ይገልጻሉ፡፡ በመሆኑም የእመቤታችን ፅላት አውጥተው ለመገለገል አስበው በድርቅ በመመታታቸው የሚቀድስላቸው ቀሳውስት መቅጠር አልቻሉም ፡፡ ያው ያላቸው አንድ ቄስ ብቻ ስለሆነ እሁድ እሁድ ኪዳን አድርሶ ጸበል እረጭቶ ይሰዳቸዋል፡፡ ቅዳሴ አይቀደስም ስጋወደሙን የሚያቀብላቸው ቄስ የለም ሲሞቱም አብዛኛውን ጊዜ ፍትሀት አይደረግም፡፡ የእመቤታችን ፅላትም የተቀመጠው በግለሰብ ቤት እንደሆነ ነው የነገሩኝ በይኔም ተመልክቸዋለሁ፡፡ ታዲያ እነዚህ ምእመናን ድረሱልን! በውኑ እነ አቡነ ተክለ ሀይማኖት የሉምን? እነ አባጊዎርጊስ አባፅጌ ድንግል የሉምን? የድንግል ልጆች የሉምን?( ሰኔ ጎልጎታን የሚደግማት የለምን?(፣ እያሉ ጥሪአቸውን በእመቤታችን ስም ያስተላልፋሉ፡፡ በውኑ እናንተ ባማረ ቤታችሁ ሳላችሁ የእመቤታችን ፅላት ግለሰብ ጎተራ ውስጥ መቀመጥ አግባብ ነውን?(፣ በውኑ እግዚአብሄር በዚህ ጊዜ እንዲህ ተናገረ የኪሳችሁን ገንዘብ እየሰበሰባችሁ የሰማይ ቤታችሁን ስሩበት ያለው ለእንደዚህ አይነት ችግር ነው ፡፡ የደብሩ ምመናን በ2009 አ.ም ለመስራት በአባይ ወንዝ ወርደን እንጨቱን እንቆርጣለን ተሸክመንም እናመጣለን ቢያንስ እንኳ 120 ቆርቆሮ የምትሆን ለመስራት አቅደዋል፡፡ ስለዚህ ወገኖቸ መቸም የእመቤታችን በረከት ያልደረሰለት የለም ስለዚህም ነገር ቤቷን ለመስራት የታደለ ሰው አስራት በኩራቱን ዛሬ እንዲያወጣላት ትጠይቀናለች ፡፡ስለዚህም የባይተዋር ማርያምን ቅዳሴ ቤቷን ለመሰራት የማርያም ሰራዊት ልንሆንላት ይገባናል አይደለም ቤቷን በገንዘባችን ይቅርና ስለ ስሟ ብለን ቀኑን ሙሉ እንነቀፍላታን እንታረድላታለን ፡፡
እንግዲህ በግል ለመርዳት የሚፈልግ ካለ ወይም
በማህበር ለመስራት የሚወድ ካለ
ሀዊረ ህይወት የሚያዘጋጅ ካለ
በስልክ ቀጥር 0924109319 ወይም የደብሩን አንድ ቅንጣት ቄስ በስልክ ቁጥሩ 0972432180 ላይ በመደወል ማጣራት ይችላሉ
እንደ አቅመዎት በሙዳየ ምፅዋት ለመደገፍ የሚፈልግ በደብሩ በተከፈተ ባንክ ቁጥር 10000175438053 መምሬ ቢያዝን ቀለመወርቅ ብለው ለሰማይ ቤተዎት ማስገባት ይችላሉ፡፡
ወደፊት ከሀገረ ስብከቱ የተጠየቀውን የፈቃድ ደብዳቤ እንደደረሰን እንለጥፍላችኋለን
ቸር ያሰንብተን

አብረው የሚሟሉ ቁሳቁሶች አጠቃላይ ለቅዳሴ የሚያስፈልጉ ቁሳቁስን ይመለከታል