ረቡዕ 15 ጁን 2016

                         ቅድስት አፎሚያ

በወርኃ ሠኔ መታሰቢያ ከሚደረግላቸው ቅዱሳን መካከል የእግዚአብሔር ወዳጅ የአስተራኒቆስ ሚስት የቅድስት አፎምያን አንዱ ነው፡፡

ቅድስት አፎምያ  እግዚአብሔርን ከሚወድ ባለቤቷ ጋር እግዚአብሔርን ስታገለግለው የኖረች ሴት ነበረች፡፡ በየወሩ በ29 ቀን የጌታችንን የልደቱን፣ ወር በገባ በ21 የእመቤታችንንና ወር በገባ በ12 የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ እያደረጉ ነዳያንን ይጎበኙ እንደነበር ታሪካቸው ይነግረናል፡፡

ባለቤቷ አስተራኒቆስ ከዚህ ዓለም የሚያርፍበት ጊዜ እንደደረሰ ባወቀ ጊዜ ይሰጡት የነበረውን ምጽዋት እና የሦስቱን በዓላት መታሰቢያ ማድረግ እንዳታስታጉል ከአደራ ጋር አዘዛት፡፡ እሷም የመልአኩን የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል ያሥልላት ዘንድ ባለቤቷን ጠይቃ አሠርቶ ሰጣት፡፡ በከበረ ቦታም አክብራ አኖረችው፡፡

ባሏ ካረፈ በኋላ ያዘዛትን መንፈሳዊ ሥራ ከወትሮው አስበልጣ መሥራት ቀጠለች፡፡ የሰው ልጆች ጠላት የሆነው ሰይጣንም በመልካም አገልግሎት ስትበረታ ባያት ጊዜ ዝም ብሎ ሊተዋት አልወደደም፡፡ በመጀመሪያ ባል ሳታገባ ማገልገሏን ትታ፣ ሌላ ባል አግብታ፣ ልጅ ወልዳ እንድትኖር በብዙ ማባበል ጠየቃት፡፡ ባሏ መንግሥተ ሰማያትን ስለወረሰ ምንም ምጽዋት እንደማይሻ አስመስሎ ነገራት፡፡

ቅድስት አፎምያ ግን ዳግመኛ ትዳር ላለመመሥረት ቃል ኪዳን እንደገባች ርግብንና ዖፈ መንጢጥን አብነት አድርጋ፤ እነሱ እንኳ በሕይወት ዘመናቸው ከአንድ ባል ውጪ ሌላ ባል እንደማያውቁ በመጥቀስ አሳቡን እንደማትቀበለው ገለጸችለት፡፡ ሰይጣንም አስመሳይነቱ አላዋጣ ሲለው ማንነቱን ቀይሮ ሊያንቃት ቢሞክር የእግዚአብሔርንና የቅዱስ ሚካኤልን ስም ጠርታ አባረረችው፡፡ እሱም ተመልሶ መጥቶ እንደሚያጠፋት ዝቶባት እንደአቧራ በኖ፤ እንደ ጢስም ተኖ ጠፋ፡፡

በሠኔ ፲፪ ቀን የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ እያዘጋጀች ሳለች ሰይጣን ብርሃናዊ መልአክ መስሎ መጣ፡፡ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል እንደሆነ ገልጾ የመጀመሪያውን የመሰለ ከንቱ ምክሩን አሰማምሮ አቀረበላት፡፡ አሳቡንም የእግዚአብሔር ፈቃድና አሳብ እንደሆነ አድርጎ ለማሳመን ሞከረ፡፡ ሰይጣን አስቀድሞ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በገዳመ ቆሮንቶስ መጻሕፍትን እየጠቀሰ እንደተፈታተነው ሁሉ ቅድስት አፎምያንም ለማሳመንም አብርሃምን፣ ይስሐቅን፣ ያዕቆብን፣ ዳዊትን የመሳሰሉ ደጋግ አባቶችን ታሪክ እየጠቀሰ ወደ ትዳር እንድትገባ ደጋግሞ ወተወታት፡፡

ቅድስት አፎምያም በእግዚአብሔር ኃይል ጸንታ በቅዱስ ሚካኤልም ተራዳኢነት ታምና “የእግዚአብሔር መልአክ ከሆንክ መንፈሳዊ ማረጋገጫህ የሆነው የመስቀል ምልክት የታለ?” በማለት በምድራዊ ንጉሥና በጭፍራው መካከል የሚኖርን የጋራ መግባቢያ መንገድ ዋቢ አድርጋ ጠየቀችው፡፡

ለጊዜው “በኛ በመላእክት ዘንድ እንዲህ አይደለም” ብሎ ሊሸነግላትና አቋሟን ሊያስቀይራት ሞከረ፡፡ ከቤቷ ያለ የቅዱስ ሚካኤል ሥዕል ላይ ያለውን ምልክት አብራርታ የእሱ ግን ከዛ ጋር አንድነት እንደሌለው አረጋገጠችበት፡፡ ከቤቷ ላለው ለቅዱስ ሚካኤል ሥዕል እጅ እንዲነሣ ጠየቀችው፡፡ በዚህ ጊዜ መልኩ ወደ ትክክለኛ ማንነቱ ተለወጠና ጨለማ ለብሶ እየዛተ አነቃት፡፡ ቅድስት አፎምያም የከበረ መልአክ ቅዱስ ሚካኤልን “ድረስልኝ” እያለች በጠራችው ጊዜ መልአኩም ፈጥኖ በመድረስ ከሰይጣን እጅ አዳናት፡፡

የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም ለሰይጣኑ ተገቢውን ቅጣት ሰጥቶ ቅድስት አፎምያን ባረካት፡፡ የዕረፍት ቀኗ በዚህ ቀን መሆኑን ነግሮ ቤቷን እንድታዘጋጅ አዘዛት፡፡ የበዓሉን ዝግጅት አከናውና ሥጋ ወደሙን ተቀብላ ኤጲስ ቆጶሱን ካህናቱን እንደየመዓርጋቸው ጠርታ በቤቷ አክብራ ተቀላ አስተናግዳ ለነዳያንና ለጾም አዳሪዎች በኤጲስ ቆጶሱና በካህናቱ እጅ ገንዘቧን መጽውታ መንገዷን አሳመረች፡፡ ስለ ኃጢአቷ እንዲጸልዩላት ተማፅና በፊታቸው ተንበርክካ ጸለየች፡፡ ባሏ ያሠራላትን የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል አቅፋ ስማ ከተማጸነች በኋላ ሠኔ ፲፪ ቀን በሰላም ዐረፈች፡፡

ይህች የታመነች ቅድስት አፎምያ በሰላም እስክታርፍ ጊዜ ድረስ የተጓዘችበትን መንፈሳዊ ጎዳና አስተውለን ይሆን? አስቀድማ ከባሏ ጋር አንድ ሆና በታማኝነት ፈጣሪዋን አገለገለችው፡፡ በኋላም የባሏን ኑዛዜ አክብራ በሁለተኛ ትዳር ራስዋን ማጠላለፍ አልፈለገችም፡፡ በጎ ሥራ አብልጣ በመሥራት እግዚአብሔርን ደስ ለማሰኘት ተፋጠነች እንጂ፡፡

ሰይጣን ልጅ አለመውለዷን ተጠቅሞ ያቀረበላትን የጋብቻ ጥያቄ ውድቅ በማድረግ “መንፈስን ሁሉ አትመኑ፤ መናፍስት ከእግዚአብሔር እንደሆኑ መርምሩ” ተብሎ በቅዱሳት መጻሕፍት የታዘዘውን መመሪያ ተጠቅማ ሰይጣንን በተወክሎ እግዚአብሔር ተቃውማ አሸነፈችው፡፡ የቅዱስ ሚካኤልን ርዳታ ያገኘችውና በሰላም ዐርፋ ወዳገለገለችው እግዚአብሔር በክብር የሔደችው በጽናት ተጋድላ ነው

በረከ'ቸው ይደብን

                         ቅድስት አፎሚያ

በወርኃ ሠኔ መታሰቢያ ከሚደረግላቸው ቅዱሳን መካከል የእግዚአብሔር ወዳጅ የአስተራኒቆስ ሚስት የቅድስት አፎምያን አንዱ ነው፡፡

ቅድስት አፎምያ  እግዚአብሔርን ከሚወድ ባለቤቷ ጋር እግዚአብሔርን ስታገለግለው የኖረች ሴት ነበረች፡፡ በየወሩ በ29 ቀን የጌታችንን የልደቱን፣ ወር በገባ በ21 የእመቤታችንንና ወር በገባ በ12 የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ እያደረጉ ነዳያንን ይጎበኙ እንደነበር ታሪካቸው ይነግረናል፡፡

ባለቤቷ አስተራኒቆስ ከዚህ ዓለም የሚያርፍበት ጊዜ እንደደረሰ ባወቀ ጊዜ ይሰጡት የነበረውን ምጽዋት እና የሦስቱን በዓላት መታሰቢያ ማድረግ እንዳታስታጉል ከአደራ ጋር አዘዛት፡፡ እሷም የመልአኩን የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል ያሥልላት ዘንድ ባለቤቷን ጠይቃ አሠርቶ ሰጣት፡፡ በከበረ ቦታም አክብራ አኖረችው፡፡

ባሏ ካረፈ በኋላ ያዘዛትን መንፈሳዊ ሥራ ከወትሮው አስበልጣ መሥራት ቀጠለች፡፡ የሰው ልጆች ጠላት የሆነው ሰይጣንም በመልካም አገልግሎት ስትበረታ ባያት ጊዜ ዝም ብሎ ሊተዋት አልወደደም፡፡ በመጀመሪያ ባል ሳታገባ ማገልገሏን ትታ፣ ሌላ ባል አግብታ፣ ልጅ ወልዳ እንድትኖር በብዙ ማባበል ጠየቃት፡፡ ባሏ መንግሥተ ሰማያትን ስለወረሰ ምንም ምጽዋት እንደማይሻ አስመስሎ ነገራት፡፡

ቅድስት አፎምያ ግን ዳግመኛ ትዳር ላለመመሥረት ቃል ኪዳን እንደገባች ርግብንና ዖፈ መንጢጥን አብነት አድርጋ፤ እነሱ እንኳ በሕይወት ዘመናቸው ከአንድ ባል ውጪ ሌላ ባል እንደማያውቁ በመጥቀስ አሳቡን እንደማትቀበለው ገለጸችለት፡፡ ሰይጣንም አስመሳይነቱ አላዋጣ ሲለው ማንነቱን ቀይሮ ሊያንቃት ቢሞክር የእግዚአብሔርንና የቅዱስ ሚካኤልን ስም ጠርታ አባረረችው፡፡ እሱም ተመልሶ መጥቶ እንደሚያጠፋት ዝቶባት እንደአቧራ በኖ፤ እንደ ጢስም ተኖ ጠፋ፡፡

በሠኔ ፲፪ ቀን የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ እያዘጋጀች ሳለች ሰይጣን ብርሃናዊ መልአክ መስሎ መጣ፡፡ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል እንደሆነ ገልጾ የመጀመሪያውን የመሰለ ከንቱ ምክሩን አሰማምሮ አቀረበላት፡፡ አሳቡንም የእግዚአብሔር ፈቃድና አሳብ እንደሆነ አድርጎ ለማሳመን ሞከረ፡፡ ሰይጣን አስቀድሞ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በገዳመ ቆሮንቶስ መጻሕፍትን እየጠቀሰ እንደተፈታተነው ሁሉ ቅድስት አፎምያንም ለማሳመንም አብርሃምን፣ ይስሐቅን፣ ያዕቆብን፣ ዳዊትን የመሳሰሉ ደጋግ አባቶችን ታሪክ እየጠቀሰ ወደ ትዳር እንድትገባ ደጋግሞ ወተወታት፡፡

ቅድስት አፎምያም በእግዚአብሔር ኃይል ጸንታ በቅዱስ ሚካኤልም ተራዳኢነት ታምና “የእግዚአብሔር መልአክ ከሆንክ መንፈሳዊ ማረጋገጫህ የሆነው የመስቀል ምልክት የታለ?” በማለት በምድራዊ ንጉሥና በጭፍራው መካከል የሚኖርን የጋራ መግባቢያ መንገድ ዋቢ አድርጋ ጠየቀችው፡፡

ለጊዜው “በኛ በመላእክት ዘንድ እንዲህ አይደለም” ብሎ ሊሸነግላትና አቋሟን ሊያስቀይራት ሞከረ፡፡ ከቤቷ ያለ የቅዱስ ሚካኤል ሥዕል ላይ ያለውን ምልክት አብራርታ የእሱ ግን ከዛ ጋር አንድነት እንደሌለው አረጋገጠችበት፡፡ ከቤቷ ላለው ለቅዱስ ሚካኤል ሥዕል እጅ እንዲነሣ ጠየቀችው፡፡ በዚህ ጊዜ መልኩ ወደ ትክክለኛ ማንነቱ ተለወጠና ጨለማ ለብሶ እየዛተ አነቃት፡፡ ቅድስት አፎምያም የከበረ መልአክ ቅዱስ ሚካኤልን “ድረስልኝ” እያለች በጠራችው ጊዜ መልአኩም ፈጥኖ በመድረስ ከሰይጣን እጅ አዳናት፡፡

የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም ለሰይጣኑ ተገቢውን ቅጣት ሰጥቶ ቅድስት አፎምያን ባረካት፡፡ የዕረፍት ቀኗ በዚህ ቀን መሆኑን ነግሮ ቤቷን እንድታዘጋጅ አዘዛት፡፡ የበዓሉን ዝግጅት አከናውና ሥጋ ወደሙን ተቀብላ ኤጲስ ቆጶሱንና ካህናቱን እንደየመዓርጋቸው ጠርታ በቤቷ አክብራ ተቀበለቻቸው፡፡ ለነዳያንና ለጾም አዳሪዎች በኤጲስ ቆጶሱና በካህናቱ እጅ ገንዘቧን መጽውታ መንገዷን አሳመረች፡፡ ስለ ኃጢአቷ እንዲጸልዩላት ተማፅና በፊታቸው ተንበርክካ ጸለየች፡፡ ባሏ ያሠራላትን የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል አቅፋ ስማ ከተማጸነች በኋላ ሠኔ ፲፪ ቀን በሰላም ዐረፈች፡፡

ይህች የታመነች ቅድስት አፎምያ በሰላም እስክታርፍ ጊዜ ድረስ የተጓዘችበትን መንፈሳዊ ጎዳና አስተውለን ይሆን? አስቀድማ ከባሏ ጋር አንድ ሆና በታማኝነት ፈጣሪዋን አገለገለችው፡፡ በኋላም የባሏን ኑዛዜ አክብራ ምንም እንኳን ኃጢአት ባይሆንባትም በሁለተኛ ትዳር ራስዋን ማጠላለፍ አልፈለገችም፡፡ በጎ ሥራ አብልጣ በመሥራት እግዚአብሔርን ደስ ለማሰኘት ተፋጠነች እንጂ፡፡

ሰይጣን ልጅ አለመውለዷን ተጠቅሞ ያቀረበላትን የጋብቻ ጥያቄ ውድቅ በማድረግ “መንፈስን ሁሉ አትመኑ፤ መናፍስት ከእግዚአብሔር እንደሆኑ መርምሩ” ተብሎ በቅዱሳት መጻሕፍት የታዘዘውን መመሪያ ተጠቅማ ሰይጣንን በተወክሎ እግዚአብሔር ተቃውማ አሸነፈችው፡፡ የቅዱስ ሚካኤልን ርዳታ ያገኘችውና በሰላም ዐርፋ ወዳገለገለችው እግዚአብሔር በክብር የሔደችው በጽናት ተጋድላ ነው፡፡

ሰኞ 6 ጁን 2016

፠፠፠እርሱ ያከበራቸውን የማያከብር ይፀፀታል መዝ፡33:21፠፠፠ ፀፀቱም ድህነት የለውም

አዲግራት ላይ ችግር እንዳለ ይታወቃል እንዲህ አይነቶችን በተሀድሶ ስር ያሉ አቀንቃኞችን እየጋበዙ ያሉቱ እዛው ውስጥ ያለው ፌዝ ዋን የሚባለው ድብቁ ሴራ ነው ይሄውም እዛው ውስጥ እያሉ እንዲገለበጡ እና እዛው ጨርሰው እንዲወጡ ስለሚያስችላቸው ነው በዚህም አይነት የግቢ ጉባኤ አመራር አካላት በማህበሩ የተመረጡ አለመሆናቸው ቀጥታ በአፈ ቀላጤነት የሚገቡ እና ከሰንበት ትምህርት ቤት ወጥተው የሚመጡ ተማሪዎች በአብዛኛው ለዚህ አይነት ነገር የተጋለጡ ናቸው ፡፡ ሰንበት ተማሪዎቹ አስተዳደጋቸው ጋጠ ወጥነት ያለው ሲሆን ግቢ ጉባኤም ገብተው ተመሳሳይ ስራ ነው የሚሰሩትና ከዚህም አንፃር ነው ሌላው የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ነው ማህበሩ በርግጥ ያለውድ በግድ ገብቶ ይሰራል ምክንያቱም ሀላፊነቱ በቅዱስ ሲኖዶስ አማካኝነት ስለተቀበለ ነውና ሊቀ ጳጳሱ ፈቀዱም አልፈቀዱም ምንም አያነጋግርም አስፈላጊውን ቁሳቁስ ማሟላት ብቻ ነው የሚጠበቀው ከእኛ ግን እንዲህ የተካረረ ነገር ላለመፍጠር መግባባት ላይ ይደረሳል ተብሎ ነው የሚታሰበው ፡፡ ከምንም በላይ ግን ግቢ ጉባኤ በሀገረ ስብከቱ ሰንበት ት/ቤት ስር መውደቅ እንደሌለበት ነው የማስበው ምክንያቱም ሰ/ት/ቤቶች አብዛኞቹ ከተሀድሶአውያን ነፃ አይደሉም ይሄ ይሰመርበት፡፡
ሌላው ከዘማሪው መጋበዝ ጋር ተያይዞ ስለክርስቶስ ተሰበከ ፡ኦርቶዶክስ ክርስቶስን አትሰብክም ፃድቃንን ነው፡ ገሌመሌ እያልን ለምንወራከብ ወጣቶች በመጀመሪያ የክርስቶስ ነኝ የሚል ሰው ስለፃድቃንና ስለ ክርስቶስ ዝምድና ማጥናት ይጠበቅበታል ፡፡ መፅሐፍ የተናገረውን አልሰማችሁምን የተባለው ዛሬምጆሮ ዳባ ልበስ አስብሏል፡፡ ምክንያቱም እንደ መፅሐፍ ቅዱስ አስተምህሮት ከሆነ፣
☞እረሱ ያከበራቸውን ማን ያዋርዳቸዋል ማንስ ከእርስቱ ያወጣቸዋል የኢየሱስ ክርስቶስ የሆነ ሁሉ እርሱ ያከበራቸውን ሊያከብር ይገባዋል ሙሴን አክብሮት የሰጠውን ህግ አላፈረሰም አጠበቀው እንጂ ለሙሴ የተሰጠው 10 ትእዛዛት አከበራቸው አስተዳደጉ እነዚህን እያከበረ ህገ ኦሪትን እየጠነቀቀ ነበረ ይላል ስለዚህ ነገር ዳዊት ፃድቃንን የሚጠላ ይፀፀታል መዝ33:21 አረ አስተውሉ ወገኖቸ ቅዱስ ጳውሎስስ ፃድቃን እንደሚፈርዱ አታውቁምን እያለን አረ ተው ወገኖቸ ያውስ መዝሙረኛው ይትአየን መልአከ እግዚአብሔር አውዶሙ ለእለ ይፈርህዎ ወያድህኖሙ መዝ 33:7 እያለ የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰወች ዙሪያ ይረብባል ያድናቸውማል፡፡ እያለን አረ ተው ወገኖቸ አስተውሉ ተው ግድ የላችሁም እንዲህ ማወቅ ማንበብ እየቻልን በጨለማ መጓዝ እስኪ መጀመሪያ ቢጠቅመንም ባይጠቅመንም እናንብብ ከዛ እናስተውል ከዛ የሰማይ የምድር አምላክ እባክህ ተናገረኝ አባክህ አናግረኝ እንበለው እንደ አብርሃም ከዛ እኛ ለጆቹን የሚወድ አምላክ ቸር ነውና ልጀ ና ይላል አረ ተው እዚህ ስንሰዳደብ ነፍሳችንን ሲኦል በላቻት ክእስቶስን መስበክ ማለት እኮን እሱ ባመለከተው መሄድ መኖር ነበረ እነዚያ የኖሩት አብነት አይሆኑንም እንዴ ከሀዋርያት ጀምሮ እነ ዲያቆን እስጢፋኖስ ተሰቅሎ ስለእውነት ሲል የአደባባይ የድንጋይ እራት ሆኖ ሳለ እኛ እዚህ ለመሞት መታገል ? ምን አለበት ሰፋ አድርገን ብናስብ አሁንም ጊዜው ቅርብ ነው ልባችን ይሻት የክርስቶስ ፍቅር በልባችን ሴቃ ውስጥ ይግባ ከዚ እንዴት ብየ ልምጣ እንበለው በራሳችን ማስተዋል መጓዙ ይብቃ ! በነገሩስ ላይ ስለ ቅዱሳን አከባበር ስለ ክርስቶስ አመላለክ እንደው መፅሐፉ እኮ ይመሰክርብናል እናንበው መጀመሪያ ለሁሉም ስርዓት ይኑረው አይደል የተባለው በቅዱስ ጳውሎስ አረ ተው ወገኖቸ እየውላችሁ መጀመሪያ የክርስቶስ ፍቅር በውስጣችን ሲያድር መከራ ይበዛብናል ስጋና ነፍስ ይጨነቃሉ እናንተ እና እኔ ጭንቀት የያዘን እርስ በርስ ነው ይህ ውሸታሙ ውጫዊ ፍቅር ነው ይሄ ደግሞ አፍ ይጠው ለሞት የተባለው እንጂ ለበረከት አይደለም፡፡ የክርስቶስ ፍቅር ሲይዘን ግን መጀመሪያ ከውስጣችን ከፍተኛ ጭቅጭቅ ይነሳብናል ስጋ እኔ አውቃለሁ እኔ በምልሽ መንገድ ሂጅ ብላ ትሞግታለች፡፡ ነፍስ ደግሞ እርይ አይሆንም እኔ ነኝ የማውቀው መንገዱን እሳት ልታስበይኝ ነው ወዮ ለኔ አንቺስ ለትንሽ ጊዜም ቢሆን አፈር ወስጥ ነሽ እኔ ዘላለሜን የእሳት ባህር ውስጥ ገብቸ ልኖር ነውን ጌታየ እኮን እንዲህ አይደለም ያለው ለዚች ለትንሽ ዘመን ለምታለፈው ዘመንሽ ብለሽየዘላለም ቤትሽን እንዳታጭ ነው እኮ ያለው......... ወዮ እየተባባሉ ሙግት ከባድ ይሆናል፡፡ ነፍስ ያቸነፈች እንደሆነ አሁን ክርስቶስን ስትጣራ መንገዱን አሳየን በየት በኩል ነው ስጋን ረትቸ አቀረብኳት ትላለች፡፡ በዚህ ጊዜ አምላክ በወደደው መንገዱን እንደተናገረ ወደቀደመችው ቀጭን መንገድ ያመላክተናል ፡፡ልብ በሉ ቅዱስ ማቴዎስ የጥፋቱ መንገድ ሰፊ ነው እንዳለን አትርሱ ከዛም ያች መንገድ እንደ ጭራ የቀጠነች መከራ የበዛባት ነች ተድላ ደስታ ወዳለበት ቦታ ግን ሳታሳስት ታደርሳለች ችግሩ ግን ከዛች መንገድ መግባት አቅም ይጠይቃልነው ፡፡እኔና እናንተ የፈለግነው በአለም ላይ ዘና ብለን ፈርሰስ ብለን ከዛ ደግሞ የሰማዩን እናስባለን አይቻልም መፅሐፉ ነው የሚለው፡፡ ቅዱስ ማቴዎስ ለሁለት ጌቶች መገዛት አይቻልም አላለንም? ዞር ብለን እናንበው አስኪ ምን እንዳለን ስለዚህ አሁን በዚህ ገፅ መሰዳደብ ለፍርድ መዘጋጀት ነው ከሱ ጋር ያሉትን ብንሰድብ ምንም አይመጣባቸውም አንድ ጊዜ መረጣቸውና ወሰዳቸው፡፡ ባልና ሚስት አንድ አልጋ ተኙ አንደኛው ተወሰደ አንደኛው ቀረ የተወሰደው ለክርስቶስ ብቁ የሆነ ነው፡ የቀረው ደግሞ እነደዚህ እንደኔ ዘመኑን በከንቱ ያሳለፈው ነው እሱ ለሲኦል አበጋዝ ተሰጠ ምን ይደረግ አሁን እንደዚህ ስል ተረት ተረት አይመስልም ? አው የክርስቶስ ነገር ላመኑት ለተቀደሱት በመከራው ውስጥ ላለፉት ፍቅሩ አገብሯቸው በገደል በዱር ለተወረወሩት ነው እውትነቱ እንጂ፡ ስለዚህ ከማስታረቅ አኳያ ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋ ትላላችሁ ስለዚህ አንብቡ ሁሉም ክርስቶስ ክርስቶስ ይላል ከማለት ይልቅ ጠጋ ብለን ጸጥ ብለን ማነህ ምን ብየ ላምልክህ? እንበለው እርስ በርሳችን ሳንዋደድ እኔ የክርስቶስ ነኝ ማለት ከንቱነት ነው እውነት መናገር እየቻልን እውነትን ትተን በሀሰት መንገድ እየነጎድን የክርስቶስ ነኝ ማለት አይቻልም፡፡ ወንድም እህታችን በቂም በውሸት እኔ እበልጥ ብለን ድብን አደርገን ከፈለገ ከፈለገች አፈር ለምን አይግጥም አትግጥም እያልን ክርስቶስ ይጠብቀናል ያድነናል ማለት ከንቱነት ነው ምክንያቱም የነዚያን ውድቀት ወደናልና መሰናክል ሆነናል ፡ከምንሆን ግን ድንጋይ ታስሮብን ወደ ጥልቅ ባህር መወርወር ይሻላችሗል ነው ያለው ንጉሰ ነገስት ክርስቶስ ስለዚህ እማፀናችሗለው በቀዳሚ አለመሰዳደብ በቀጣይ እኔ እግዚአብሔር ነኝ አለም ሳይፈጠር አስቀድሜ ነበርኩኝ እኔና አብ አንድ ነን እናንተ ቅዱሳን ሳላችሁ በአለም ላይ ትፈርዳላችሁ ለአብረሀም ቃል የገባ የፃድቃን መታሰቢያ ለዘላለም ነው ያለውን አምላክ ቅዱስ ማቴዎስ በአንቀፀ ብፁአን የተነተነውን ደጋግመን በማንበብ ሀይማኖት ከምግባር ጋር አስተባብሮ ማወቅ ነው የሚሻለው ውድድሩ ቢቀርብን ይሻለናል ......... ሰላም

[☞ተአምረ ማርያም እነሆ እፁብ ድንቅ ነገር☜]✞✞✞

አነንዲት በእመቤታችን ስእል ተጊጣ የተሰራች ቤተክርስቲያን ነበረች ከእለታት አንድ ቀን የሚጠብቃትና በር የሚከፍተው ሰው ነበረ እናም ይሄ ሰው አንዴ ቀን ከሴት ጋር ነበረና በሌሊተ ሰአት ተነስቶ ደወል ከደወለ በሗላ እንደለመደው በሩን ሊከፍት ሄደ ከመቃወም አጠገብ ሳለ በሩን በእጁ ሳይነካው ከወደጎኔ በበትሩ ነካኝ አለ ዘወር ብየ ሳየው መልአኩ መሆኑን ነግሮ ይህችን በር ነክተሀት ቢሆን ኖሮ በዚህ ሰይፍ ከሁለት ነበረ የማደርግህ አለው በድንጋጤም ተመለሰ ከዛም ይህ ሰው የሴቶች መርገም በእስኪቱ መጣበት እንደሴቶች መርገመ ደም መታው በዚህም ምክንያት ተነስቶ የእመቤታችን ተአምር አገር ላገር እራሱን አዋርዶ መሠከረ እድሜ ልኩን ከሰዉ ተገልሎ ኖረ :: እንግዲህ የእግዚአብሔርን ቤት በድፍረት የምንቀርብ ወዮልን የተቀደሰውን የምናረክስ መርገማችን ተፅፎብናል መንገዳችን ተዘግቶብናል በፍፁም እውነትነትና ትህትና በንፅህና ሊሆን ይገባናል ስጋውን ደሙን የምናረክስ ወዮልን በመደፋፈር ከቀረብነው ይልቅ በትህትና የተታታው እርሱ ቀድሞ በምግባሩ ተባረከ በተቀበለውም ጊዜ በረከቱ እጅግ ድንቅ
እንግዲህ የአማኑኤል ቤት የእውነት አምድ ነው
የእመቤታችን ምልጃና በረከት ከሚፈሯት ከባለሟሎቿ ጋር ለዘላለም ፀንቶ ይኑር አሜን